“የአገልጋይ ገጸባህሪያት አቀራረብ ከ1990 እስከ 2010 ዓ.ም ድረስ በታተሙ የተመረጡ የሴት ደራሲያን ረጅም ልቦለዶች ውስጥ”

dc.contributor.advisorመሀመድ አሊ (ዶ.ር)
dc.contributor.authorአበበች ሀብተማርያም
dc.date.accessioned2024-06-27T13:03:33Z
dc.date.available2024-06-27T13:03:33Z
dc.date.issued2016-01
dc.description.abstractይህ ጥናት “አገልጋይ ገጸባህሪያት ከ1990 እስከ 2010 ዓ.ም ድረስ በታተሙ የተመረጡ የሴት ደራሲያን ረጅም ልቦለዶች ውስጥ” በሚል ርእስ የተከናወነ ነው፡፡ በተጠቀሱት ሃያ ዓመታት ውስጥ ከታተሙ የሴት ደራሲያን ረጅም ልቦለድ መፃህፍት ውስጥ የጥናቴ ዋና ጉዳይ በሆኑት “አገልጋይ ገጸባህሪያት” ዙሪያ ሽፋን ሰጥተዋል ብዬ ያመንኩባቸውን ሶስት ልቦለድ መጻህፍትን በመምረጥ ጥናቴን አካሂጃለሁ፡፡ ጥናቴን ያከናወንኩባቸው ረዥም ልቦለዶች ሶስት ናቸው፡፡ ፀሐይ መልአኩ በ1996 ዓ.ም ያሳተመችው “ቢስ ራሔል”፣ በ2002 ዓ.ም የታታመው የየዝና ወርቁ “የደራሲዋ ፋይል” እና በ2003 ዓ.ም የታተመው የእንዬ ሺበሺ “የገቦ ፍሬ” ጥናቱ ያተኮረባቸው ልቦለድ መጻህፍት ናቸው፡፡ ይህ ጥናት በተመረጡት ሶስት ረዥም ልቦለድ መጻህፍት ውስጥ የሚገኙ አገልጋይ ገጸባህሪያትን ወደ እዚህ ሙያ የገፋፏቸውን ምክንያቶች ያጠናሁበት ነው፡፡ በተጨማሪም አገልጋይ ገጸባህሪያትን በተመረጡት ልቦለዶች ውስጥ ስንመረምራቸው አይነታቸው ከየትኛው እንደሚመደብና አቀራረባቸው ምን እንደሚመስል መርምሬያለሁ፡፡ የሶስቱ ልቦለዶች ገጸባህሪያት ማለትም የ“ቢስ ራሔል” ራሔል ዳርጌ፣ “የደራሲዋ ፋይል” ፅዮን ታምሩ እና “የገቦ ፍሬ”ዋ ነፃነት ክብሩ ውስብስብነት የሚታይባቸውና በህይወት ውጣ ውረድ መከራቸውን ያዩ ገጸባህሪያት ናቸው፡፡ ቤተሰባዊና ማህበረሰባዊ ጫናዎቻቸውን ለማራገፍ በሚጥሩበት ጊዜ የሚደቀኑባቸውን ሌሎች ፈተናዎች እየተወጡ ወደ ስኬታቸው ለመቅረብ የቻሉ ገጸባህሪያት መሆናቸውን ከታሪኮቻቸው ተገንዝበናል፡፡ ለነዚህ ሶስት ገጸባህሪያት ምንም ነገር በቀላሉ የለም፡፡ ለሚበሉት ቁራሽ እንጀራ እንኳን ሲቸገሩ እንደ ነበር ከየልቦለዶቹ ተረድተናል፡፡ የሚፈልጓትን እያንዳንዷን ነገር ለማግኘት የሚገጥማቸው ልፋትና ጥረት አስጨናቂና አንዳንዴም አሰቃቂ ሆኖ የቀረበበት ሁኔታ አለ፡፡ ይህ ሁኔታ ደግሞ አጠቃላይ ገጸባህሪያቱ ከተሳሉበት ጊዜና ቦታ አንፃር “ለምን ሆነ?” ብለን የምንተቸው አይደለም፡፡ እንደውም የዋና ገጸባህሪያትን ውስብስብ ድርሻ አሳይተውናል፡፡
dc.identifier.urihttps://etd.aau.edu.et/handle/123456789/3267
dc.language.isoam
dc.publisherAddis Ababa University
dc.title“የአገልጋይ ገጸባህሪያት አቀራረብ ከ1990 እስከ 2010 ዓ.ም ድረስ በታተሙ የተመረጡ የሴት ደራሲያን ረጅም ልቦለዶች ውስጥ”
dc.typeThesis

Files

Original bundle
Now showing 1 - 1 of 1
No Thumbnail Available
Name:
አበበች ሀብተማርያም.pdf
Size:
844.41 KB
Format:
Adobe Portable Document Format
License bundle
Now showing 1 - 1 of 1
No Thumbnail Available
Name:
license.txt
Size:
1.71 KB
Format:
Item-specific license agreed to upon submission
Description: