የሰዋስው ትምህርት አተገባበር ውጤታማነት ከተማሪዎች ቋንቋ ዳራ አንፃር (በተመረጡ አስረኛ ክፍሎች ናሙናነት )
No Thumbnail Available
Date
2016-09-30
Authors
መሰረት በላይ
Journal Title
Journal ISSN
Volume Title
Publisher
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ
Abstract
የዚህ ጥናት ዋና አላማ በደቡብ ክልል በጉራጌ ዞን በወልቂጤ ከተማ ህዳሴ ፍሬ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሰዋስው ትምህርት አተገበባበር ውጤታማነት ከተማሪዎች ቋንቋ ዳራ አንፃር መፈተሸ ነው ፡፡ በወሌቂጤ ከተማ ከሚገኙ አራት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ዉስጥ በህዲሴ ፍሬ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በአላማ ተኮር የናሙና ዘዴ የተመረጠ ሲሆን የ10ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መምህራን ጥቂት በመሆናቸው ሁለም ተመርጠዋል እንዲሁም በብድግ ብዴግ ናሙና ዘዴየተመረጡ 120 ተማሪዎች የፅሁፍ መጠይቅ እንዲሞሉ ፣80 ተማሪዎች ፈተና እንዲፈተኑ ተደርጓል ፡፡ ከእነዚህ መረጃ ሰጪዎች በሰነድ ፍተሻ ፣በፅሁፌ መጠይቅ ፣በክፍል ውስጥ ምልከታና በፈተና መረጃዎች ተሰብስበዋል ፡፡ የሰበሰቡት መረጃዎች አይነታዊና መጠናዊ የምርምር ዘዴ በመጠቀም ተተንትነዋል፡፡ በተጠቀሱት መሳሪያዎች በመታገዝ የተሰበሰቡት መረጃዎች ተጠናክረው ባስገኙት ውጤት መሰረት የቋንቋ መምህራን የሰዋስው ትምህርት አተገባበር በሚመለከት በሰነድ ፍተሻ ፣በጽሁፌ መጠይቅ ፣በክፍል ምልከታና በፈተና አማካኝነት መረጃ ለመሰብሰብ ተሞክሯሌ፡፡ የተሰበሰቡ መረጃዎችም በማደራጀትና በመተንተን የሚከተለትን ውጤቶች ለማግኘት ተችሎል፡፡ መምህራኑ የሚዘጋጁበትን ይዘት ከተማሪዎቹ ዕድሜ የክፍል ደረጃና ከመጡበት ማህበረሰብ ጋር የመጣጣም አቅሙ አነስተኛ ሲሆን የዓላማ ዝግጅታቸውም የመስፋትና የተተግባሪነት ችግር ይታይበታል፡፡ እንዲሁም መምህራን በአብዛኛው ርቱዕ ስሌትን የሚጠቀሙ ሲሆን አተገባበራቸው አፍላቂና አሳታፉ አልነበረም ፣ የሰዋስው መዋቅርን ቅርፅ ፣ ፈቺና ማህበራዊ አጠቃቀም ለማስተማር በክፍል ውስጥና ውጭ ያለ አውዶች የመጠቀም ልምዲቸው ዝቅተኛ ከመሆኑም በላይ ድጋፍ ሲጪ መሳሪያዎችን እንደማይጠቀሙ የጥናቱ ውጤት ያሳያል ፡፡ በተጨማሪም የመምህራኑ የምጋቤ ምሊሽ አሰጣጥ ሰንመለከት ደግሞ በልምምድ ወቅት እርማት የሚሰጡ ቢሆንም የእርማት አሰጣጡ ግን ፉት ለፉት የተቀመጡና እጅ ያወጡ ተማሪዎችን ያማከለና ተዘውታሪነት የጎደለው ነበር ፡፡ እንዱሁም ተማሪዎቹ የአማርኛ ቋንቋ ሰዋስውን ለመማር ያላቸው ፍላጎት ዝቅተኛና በመማር ማስተማሩ ሂደቱም ላይ ያላቸው ተሳትፍ ዝቅተኛ እንደሆነ ለማወቅ ተችሎል ፡፡ በሰዋስው ዕውቀት መመዘኛ ፈተና ላይም የጎላ ውጤት አልታየም ፡፡ በመሆኑም ከላይ ለተጠቀሱት አተገባባር ችግሮች የመፍትሄ ሀሳቦች በማስቀመጥ ጥናቱ ተጠናቋል ፡፡
Description
Keywords
የሰዋስው ትምህርት አተገበባበር