ስነፅሁፋዊና ኢስነፅሁፋዊ ፅሁፎች የተማሪዎችን የአማርኛ ቋንቋ የአንብቦ መረዳት ክሂልን ከማሻሻል ረገድ ያለቸው ሚና (በሻምቡ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በአስረኛ ክፍልተተኳሪነት)

No Thumbnail Available

Date

2023-06

Journal Title

Journal ISSN

Volume Title

Publisher

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ

Abstract

የጥናቱ ዋና አላማ ስነፅሁፋዊና ኢስነስሁፋዊ ፅሁፎች የተማሪዎችን የአማርኛ ቋንቋ አንብቦ መረዳት ኪሂልን ከማሻሻል ረገድ ያላቸውን ሚና በንፅፅር መመርመር ነው፡፡ የጥናቱ ንድፍ ከፊል ሙከራዊ ነው፡፡ የጥናቱ ተሳታፊዎች በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ሻምቡ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2015 ዓ.ም በ10ኛ የክፍል ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ከሚገኙት 915 ተማሪዎች መካከል በእድል ሰጪ ናሙና ዘዴ የተመረጡ 45 ወንድና 57 ሴት በድምሩ 102 ተማሪዎች ናቸው፡፡ ጥናቱም ሁለት ተጠኚ ቡድኖችን የያዘ የሁለት ቡድን ቅድመና ድህረ ልምምድ ፈተና ተግባራዊ ያደረገ ነዉ፡፡ ለተማሪዎች የቅድመ ትምህርት ፈተና ተሰጥቷል፡፡ ለስድስት ሳምንታት በአጥኚዉ ከተማሩ በኋላ የድህረ ትምህርት ፈተናዉ ከቅድመ ትምህርት ፈተናዉ በተመሳሳይ መለክ ተዘጋጅቶ እንዲፈተኑ ተደርጓል፡፡ ከዚያም ከተማሪዎች በቅድመ ትምህርትና ድህረ ትምህርት ፈተናዎችና በፅሁፍ መጠይቅ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች ተሰብስበዋል፡፡ መረጃዎችም መጠናዊ የምርምር ዘዴን በመጠቀም በነፃናሙናና ዳግም ልኬታ ቲ ቴስት ተተንትነዋል፡፡ በሁለቱም መረጃ መሰብሰቢያዎች አማካኝነት የተገኙ መረጃዎች በድህረ ትምህርት ፈተና አማካይ ውጤቶች የስነፅሁፍ 15.53 የኢስነፅሁፍ ቡድን 7.82 መካከል በነፃ ናሙና ቲ ቴስት ትንተናው መሰረት ጉልህ ልዩነት(p<0.05) ታይቷል፡፡ ይህም በስነፅሁፋዊ ፅሁፍ የተማሩ ተማሪዎችን የአንብቦ መረዳት ክሂልን እንደሚያጎለብት አመላክቷል፡፡ በስነፅሁፈዊና ኢስነፅሁፋዊ ፅሁፍ የተማሩ ተማሪዎች የፅሁፍ መጠይቅ የድህረ ትምህርት አማካይ ውጤቶች መካከልም የስነጽሁፍ ቡድን ተማሪዎች 29.12 የኢስነፅሁፍ ተማሪዎች 23.29 መካከል በነፃናሙና ቲ ቴስት ትንተና ጉልህ የሆነ ልዩነት (p<0.05) የአሳየና የማንበብ ችሎታን የሚፈጥር ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በአንጻሩ ኢስነፅሁፋዊ ተማሪዎች የፅሁፍ መጠይቅ አማካይ ዉጤት እንዳመለከተዉ በተማሪዎች የአማርኛ ቋንቋ አንብቦ የመረዳት ክሂል ተነሳሽነት ላይ የተለየ ለውጥ የሚያመጣ አለመሆኑ በጥናቱ ተረጋግጧል፡፡ በአጠቃላይ በስነፅሁፋዊና ኢስነፅሁፋዊ ፅሁፎች የተማሩ ተማሪዎች የድህረትምህርት ፈተና በነፃናሙና ቲቴስት ስሌት መሰረት በስነፅሁፋዊ ፅሁፍ የተማሩት ተማሪዎች የአንብቦ መረዳት ክሂል ችሎታ ጉልህ ልዮነት (p<s0.05) አሳይቷል፡፡ ምክንያት በተማሪዎች የማንበብ ችሎታ ላይ የታየው ለውጥ በስነ-ፅሁፋዊ ፅሁፍ የመጣ መሆኑን የጥናቱ ውጤት አመላክቷል፡፡

Description

Keywords

አማርኛ ቋንቋ አንብቦ መረዳት ኪሂል

Citation