የሰዋስው ትምህርት ይዘቶች አቀራረብና አደረጃጀት ግምገማ (ለኢ-አፈ ፈት ተማሪዎች በተዘጋጁት የ7ኛና 8ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መጻህፍት ተተኳሪነት)

No Thumbnail Available

Date

2023-10

Journal Title

Journal ISSN

Volume Title

Publisher

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ

Abstract

የዚህ ጥናት ዋና ትኩረት በኦሮሚያ ክልል በ2014ዓ.ም ኢ-አፈ ፈት ለሆኑ የ7ኛና የ8ኛ ክፍል አማርኛ ቋንቋ መማሪያ መጻህፍት ውስጥ የተካተቱት የሰዋስው ትምህርት ይዘቶች አቀራረብና አደረጃጀት የሚፈትሽ ነው፡፡ ጥናቱ ጥያቄ አድረጎ በተነሳባቸው ነጥቦች ዙሪያ የቋንቋ ምሁራን ያቀርቧቸውን ንድፈ ሀሳባዊ መሠረቶች መንደርደሪያ በማድረግ በሰዋስው ትምህርት ይዘቶች አቀራረብና አደረጃጀት መርሃ ስር መነሳት ያለባቸውን ነጥቦች ለመመለከት ሞክሯል፡፡ የጥናቱ ዓብይ የመረጃ ምንጭ የሰነድ ፍተሻ ሆኖ ከተማሪዎችበፅሁፍ መጠይቅና ከመምህራን በቃለ መጠይቅ በተገኙ ምላሾችምመረጃውን ለማጠናከር ተሞክሯል ፡፡ ከዚህ የመረጃ ምንጮች የተገኙ ምላሾችም ባላቸው ተዛማጅነት አንድ ላይ እየተደራጁ በምዕራፍ አራት ስር ተተንትነዋል፡፡ ከጥናቱ የተገኘው ውጤት እንደሚያመለክተው ከይዘቶች አቀራረብ አንጻር የ7ኛና የ8ኛክፍል ውጤት ተኮር አቀራረብን ሰፊ ሽፋን የሰጠ ሲሆን የ7ኛና የ8ኛ ክፍል መማሪያ መፃህፍት ከዝርዝር ወደ አጠቃላይ አቀራረብ ላይ የበለጠ ትኩረት በመስጠት አብላጫውን ሽፋን እንዲይዙ በማድረግ የቀረቡ ናቸው፡፡ከተገቢነት አንፃርም በአብዛኛው መፃህፍቱ ለተዘጋጁላቸው ተማሪዎች ዳራዊ እውቀት፣የመስራት አቅም፣የመረዳት ችሎታ ተገቢ ያልሆኑ ቸግሮች እንዳሉባቸው ለማስተዋል ተችለዋል፡፡ከአደረጃጀት አንፃርም በ7ኛና 8ኛ ክፍል መማሪያ መፃህፍት ውስጥ የተካተቱ የሰዋስው ትምህርት ይዘቶች አብዛኞቹ ተደጋግመው የቀረቡ እንዳልሆኑና ጥልቀታቸውም እየጨመረ የመሄድ ችግር ያለባቸው እንዳሉ ተስተውሏል፡፡ በሁለቱም መማሪያ መፃህፍት መካከል ተለጣጣቂነት የሚታይባቸው ይዘቶችም እንዳሉ ሁሉ የተወሰኑት ስፋትናጥልቀታቸው እየጨመረ የማይሄዱ ይዘቶች እንዳሉ ለማየት ተችሏል፡፡

Description

Keywords

የሰዋስው ትምህርት ይዘቶች

Citation