በቴክስት ውቅር ብልሃቶች በዐማርኛ ማንበብን መማር በተማሪዎች የአንብቦ መረዳት ችሎታ ላይ ያለው ተጽዕኖ- በስድስተኛ ክፍል ተተኳሪነት

No Thumbnail Available

Date

2009-06

Journal Title

Journal ISSN

Volume Title

Publisher

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

Abstract

የጥናቱ ዋና ዓላማ በቴክስት ውቅር ብልሃቶች ማንበብን መማር በተማሪዎች የማንበብ ተነሳሽነት፣ የማንበብ ግለብቃት እምነት፣ የማንበብ ትኩረትና የአንብቦ መረዳት ችሎታ ላይ ያለውን ቀጥተኛና ኢቀጥተኛ ተጽዕኖ መፈተሽ ነው፡፡ ዓላማውን ለማሳካትም መጠናዊ ምርምር ብሎም ፍትነትመሰል የጥናት ንድፍ ተግባራዊ ሆኗል፡፡ በመሆኑም በቴክስት ውቅር ብልሃቶች፣ በብልሃትአልባ የቴክስት ውቅር እውቀትና አዘውትሮ በስራ ላይ በሚውለው የማንበብ ትምህርት አቀራረቦች ሦስት ቡድኖች ተለያይተው የአንብቦ መረዳት ትምህርትን በ12 ሳምንታት ለ24 ክፍለጊዜያት እንዲማሩ ተደርጓል፡፡ የጥናቱ ተሳታፊዎችም በደሴ ከተማ በአዲስፋና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርትቤት በ2009 ዓ.ም በመማር ላይ ከሚገኙ አራት የስድስተኛ ክፍል መማሪያ ክፍሎች ውስጥ በተራ እጣ ንሞና ዘዴ የተመረጡ ሦስት መማሪያ ክፍሎች ማለትም በብልሃት ቡድኑ 44፣ በብልሃትአልባ ቡድኑ 45፣ በቁጥጥር ቡድኑ 46 በጥቅሉ 135 ተማሪዎች ናቸው፡፡ ከተሳታፊዎቹም ቅድመትምህርትና ድህረትምህርት የአንብቦ መረዳት ውጤት፣ የማንበብ ትኩረት፣ የማንበብ ተነሳሽነትና የማንበብ ግለብቃት እምነት በፈተናዎችና በመጠይቆች አማካይነት መረጃዎች ተሰብስበዋል፡፡ መረጃዎቹም በአማካይ ውጤት፣ በመደበኛ ልይይት፣ በአበርልይይት ብሎም የድኅረት ስሌት መሰረት ባለው የHayes (2013) ፕሮሰስ ፕላግኢን ኤስ.ፒኤስ.ኤስ (Hayes PROCESS plugin SPSS) ባለትይዩ የደንጋጊ ተላውጦዎች ትንተና ሞዴል 4 ተሰልተው ተተንትነዋል፡፡ የጥናቱ ግኝቶች እንዳመላከቱትም በሌሎቹ ሁለት አቀራረቦች ከተማሩት ተማሪዎች ይልቅ በቴክስት ውቅር ብልሃቶች ማንበብን የተማሩት በአንብቦ መረዳት ውጤታቸው፣ በማንበብ ተነሳሽነታቸው፣ በማንበብ ግለብቃት እምነታቸውና በማንበብ ትኩረታቸው ጉልህ መሻሻል አሳይተዋል፡፡ እንዲሁም የቴክስት ውቅር ብልሃቶች ትምህርት በአንብቦ መረዳት ውጤት ላይ ለሚያሳድረው ተጽዕኖ የማንበብ ትኩረትና የማንበብ ተነሳሽነት ከፊል የደንጋጊነት ሚና ሲያሳዩ የማንበብ ግለብቃት እምነት ግን ደንጋጊነቱ ጉልህ ሆኖ አልተገኘም፡፡ ከጥናቱ ግኝቶች በመነሳትም በቴክስት ውቅር ብልሃቶች ማንበብን መማር የተማሪዎችን የአንብቦ መረዳት ውጤት፣ የማንበብ ተነሳሽነት፣ የማንበብ ግለብቃት እምነትና የማንበብ ትኩረት ያሻሽላል ወደሚል ድምዳሜ ተደርሷል፡፡ ከዚህም ሌላ የቴክስት ውቅር ብልሃቶች ትምህርት በተማሪዎች የማንበብ ትኩረትና የማንበብ ተነሳሽነት ላይ የሚያስከትለው መሻሻል ኢቀጥተኛ በሆነ መንገድም የአንብቦ መረዳት ውጤት ከፍ እንዲል ያደርጋል ወደሚል መደምደሚያ ተደርሷል፡፡ ከጥናቱ ግኝቶች በመነሳትም ስነትምህርታዊ የመፍትሄ ሀሳቦች ተጠቁመዋል፤ የወደፊት የምርምር አቅጣጫዎችም ተመላክተዋል፡፡

Description

Keywords

በዐማርኛ ማንበብን መማር በተማሪዎች የአንብቦ መረዳት

Citation