የ9ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መምህራን በተማሪዎቻቸው የጽሁፍ መልመጃ ላይ የሚሰጡት ጽሁፋዊ ግብረመልስ አተገባበር ፍተሻ (በሀዲያ ዞን በሌሞ ወረዳ በሹርሞ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተተኳሪነት)

dc.contributor.advisorታደሰ ሲባሞ
dc.contributor.authorብርሃነሽ ሻንቆ
dc.date.accessioned2023-12-12T07:58:45Z
dc.date.available2023-12-12T07:58:45Z
dc.date.issued2022-06
dc.description.abstractየዚህ ጥናት አጠቃላይ አላማ በሹርሞ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ9ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መምህራን በተማሪዎቻቸው የጽሁፍ መልመጃ ላይ የሚሰጡት ጽሁፋዊ ግብረመልስ ከተማሪዎቻቸው ጽሁፋዊ ስራ ጋር መመርመር ነው፡፡ በጥናቱም አይነታዊ እና መጠናዊ የምርምር ዘዴን በመጠቀም ጽሁፋዊ ግብረመልሱን ፈትሿል፡፡ በትምህርት ቤቱ የሚገኙ አራት የአማርኛ ቋንቋ መምህራን በጠቅላይ የናሙና አመራረጥ ዘዴ የጥናቱ ተሳታፊ እንዲሆኑ ተመርጠዋል፡፡ ለጥናቱ እንደ ዋና መረጃነት ያገለገሉት በመምህራን ታርመው የተመለሱት የተማሪዎች የጽሁፍ መልመጃዎች፣ የመምህራን ቃለ መጠይቅና የተማሪዎች የጽሁፍ መጠይቆች ናቸው፡፡ ታርመው የተመለሱ የጽሁፍ መልመጃዎች ከግብረመልስ አይነቶች፣ ከአሰጣጥ ስልት፣ ከትኩረት አቅጣጫና ከባህሪያት አንጻር ተተንትነዋል፡፡ በዚህም መሰረት የአማርኛ ቋንቋ መምህራን በአብዛኛው ገምጋሚ ግብረመልስን መጠቀማቸው፣ የግብረመልስ ስልቶችን በመጠኑም ቢሆን እያሰባጠሩ መጠቀማቸው፣ ቅርጽና ይዘት ላይ ትኩረት አድርገው ግብረመልስ መስጠታቸው፣ የትምህርቱን ይዘት እና አላማ መሰረት አድርገው የተመጠነ አስተያየት መስጠታቸውና ግብረመልስ የሰጡባቸው ወረቀቶች በተወሰነ መልኩ በጊዜ አለመመለሳቸውንም ጥናቱ ያሳያል፡፡ በመጨረሻም መምህራን ሁሉንም የግብረመልስ አይነቶችን እንደ አስፈላጊነታቸው እያጣመሩ ቢሰጡና ግብረመልሱም ውጤታማ እንዲሆን በጊዜው ቢሰጥና ለተማሪዎች ማስተካከል ያለባቸውን ነገር ቢጠቆም ጥሩ ነው፡፡
dc.identifier.urihttp://etd.aau.edu.et/handle/123456789/685
dc.language.isoam
dc.publisherአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ
dc.subjectየ9ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ: የጽሁፍ መልመጃ
dc.titleየ9ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መምህራን በተማሪዎቻቸው የጽሁፍ መልመጃ ላይ የሚሰጡት ጽሁፋዊ ግብረመልስ አተገባበር ፍተሻ (በሀዲያ ዞን በሌሞ ወረዳ በሹርሞ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተተኳሪነት)
dc.typeThesis

Files

Original bundle
Now showing 1 - 1 of 1
No Thumbnail Available
Name:
ብርሃነሽ ሻንቆ.pdf
Size:
2.23 MB
Format:
Adobe Portable Document Format
License bundle
Now showing 1 - 1 of 1
No Thumbnail Available
Name:
license.txt
Size:
1.71 KB
Format:
Item-specific license agreed to upon submission
Description: