በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በኢትዮዽያ ቋንቋዎችና ስነፁሑፍ ክፍል በበሳል ድርሰትና በሌሎች ኮርሶች ተማሪዎች በአማርኛ የሚያከናዉኗቸዉ የፅሀፈት ስራዎች ንጽጽራዊ ጥናት

dc.contributor.advisorዮናስ, አድማሱ
dc.contributor.authorግርማ, አዉጋቸዉ
dc.date.accessioned2020-10-30T07:10:33Z
dc.date.accessioned2023-11-09T04:04:44Z
dc.date.available2020-10-30T07:10:33Z
dc.date.available2023-11-09T04:04:44Z
dc.date.issued1988-06
dc.description.abstractይህ ጥናት በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ፤ በኢትዮዽያ ቋንቋዎችና ስነፁሑፍ ክፍል አማርኛ ዋና ትምህርታቸዉ ለሆኑ መደበኛ ተማሪዎች በሚሰጡ በበሳል ድርሰትና በሌሎች የአማርኛ ኮርሶች ዉስጥ ተማሪዎች የሚያከናዉኗቸዉ የፅሀፈት ስራዎች የሚመለከት ነዉ፡፡ ጥናቱ በአላማዉ በበሳል ድርሰት የሚደረጉት የፅህፈት ልምምዶች በሌሎች ኮርሶች ከሚከናዎኑት የፅህፈት ስራዎች ያላቸዉን መጣጣምና መደጋገፍ፤የበሳል ድርሰትና ኮርሶች በሌሎች ኮርሶች ለሚያስፈልጉ የፅህፈት ሥራዎች ይሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ ሌሎች ኮርሶች ደግሞ የጽህፈት ክሂሊን ለማዳበር የሚያደርጉትን ጥረት መርምሮ ማሳየት ነዉ ፡፡ የጥናቱን ዓላማ ከግብ ለማድረስም በበሳል ድርሰትና በሌሎች ኮርሶች የሚከዎኑ የጽህፈት ሥራዎች አይነትና ባህሪ በጽህፈት ሥራዎቹ አስፈላጊ የሆኑ የጽህፈት ክሂሎች መምህራን ለተማሪዎች ጽሁፎች ሚስጡት ምላሽ እና ሌሎች በጥናቱ ተፈላጊ የሆኑ ዝርዝር ነጥቦች ከቃለመጥይቁ ፤ከመጠይቅ፤ከኮርስ ቢጋራና መግለጫና ከተማሪ ጽሁፎች በተገኙ መረጃዎች መሰረትነት ተተንትነዋል፡፡ ከነዚህ ምንጮች የተገኘዉ የመረጃ ትንተና እንደሚያሳየን በበሳል ድርሰት ኮርሶች የሚያደርጉት የጽህፈት ልምምዶች ከዐርፍተ ነገር ምስረታ አንስቶ ሙሉ ድርሰትን በገላጭ፤ በተራኪ፤በአስረጂና በአከራካሪ ድርሰቶች እስከመከዎን ይደርሳሉ፡፡ልምምዶቹ ከተለያዩ ነገሮች (ከንባብ ፤ከስዕል፤ከተፈጥሯዊ ገፅታ) ጋር በመቀናጀት የሚቀርቡ ቢሆንም አብዛኛዉቹ ከግል ገጠመኝ ወይም ስሜት በመነሳት የሚከዎኑ ናቸዉ፡፡በነዝህ ኮርሶች የመምህሩ እርማት ከይዘት ይልቅ በቅርፅ ላይ ከፍተኛ ትኩረት ይደረጋል፡፡እርማቱም የሚሰጠዉ በአብዛኛዉ (80%) በተማሪዎች የመጨረሻዉ ጽሁፍ ላይ እንጂ በረቂቅ ጽሁፎቻቸዉ ላይ አይደለም፡፡ በሌላዉ መልኩ፤ከበሳል ድርሰት ዉጪ ባሉ ኮርሶች የሚከዎኑ ጽሁፎች የተለያዩ አይነቶች ናቸዉ፡፡ሆኖም በአብዛኛዎቹ ኮርሶች የሚፃፉት ተማሪዎች በይዘቱ (subject matter) ላይ ያላቸዉን ግንዛቤ እንዲያሳዩ ነዉ፡፡የእነዚህ ሀሳቤ ምንጭ ከባዶ ወይም ከግል ገጠመኝ ስሜት የሚነሳ አይደልም፡፡ የእነዚህ ስራዎች የሀሳብ ምንጭ ንባብ ወይም በመማር ማስተማሩ ሂደት ከኮርሱ የተገኘዉ እዉቀት ነዉ፡፡በነዚህ ኮርሶች ተማሪዎች የሚጽፋቸዉ ፁሁፎች አብዘኞቹ አይመለሱም፡፡ መምህራኑ በጽህፎቹ ላይ የሚሰጡት እርማት ባብዛኛዉ ማርክ (ቁጥር) መፃፍ ብቻ ሲሆን ፤ ስህትቶችን በማመልከት የሚደረጉት እርማቶች ከቅርፅ ይልቅ በይዘት ላይ በከፍተኛ ደረጃ የሚያተኩሩ ናቸዉ፡፡ ከነዚህ ነጥቦች አንፃር ስንመለከት በኢትዮዽያ ቋንቋዎችና ስነፁሑፍ ክፍል የጽህፈት ክሂልን በመተጋገዝና በመተባበር ለማዳበር የሚደረገዉ ጥረት ደካማ መሆኑን የመረጃዉ ትንተና አሳይቷል፡፡ ስለሆነም ከዚህ ጥናት ግኝት በመነሳት ፤የኢትዮዽያ ቋንቋዎችና ስነፁሑፍ ክፍል የተሸሉ ጸሀፊዎችን ለማፍራት ይቻለዉ ዘንድ የበሳል ድርሰት እና ሌሎች ኮርሶችን መምህራን ተሰብስበዉ የሚያወያዩትን መንገድ ክፍሉ እንዲያመቻች ፤ የድርሰት መምህራን የጽህፈት ልምምዶቹ ከግል ገጠመኝ በመነሳትና በመጨረሻዉ ዉጤት ላይ በማተኮር እንዲከወኑ ከማድረግ የጽሁፍ ሂደትን ንባብ-ምርኩዝ በሆ ስራዎች በማቀናጀት ቢያስተምሩ የተሸለ እንደሚሆን፤የልሎች ኮርሶች መምህራን የተማሪዎችን ጽሁፎች በወቅቱ አርመዉ እንዲሰጡ፤ በእርማቱም ይዘት ላይ ከማተኮር ወይም ማርክ ብቻ ከመፃፍ ሌሎች የጽሁፍ ገፅታዎችን ተመልክቶ ተማሪዎችን ድክመት ያለባቸዉን ገፅታ በማመልከት እርማታቸዉን እንዲያደርጉ በዚህ ጥናት ተጠቁማል፡፡en_US
dc.identifier.urihttp://etd.aau.edu.et/handle/123456789/22973
dc.language.isoamen_US
dc.publisherአዲስ አበባ ዩንቨርስቲen_US
dc.subjectበሳል ድርሰትና ሌሎች ኮርሶችen_US
dc.titleበአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በኢትዮዽያ ቋንቋዎችና ስነፁሑፍ ክፍል በበሳል ድርሰትና በሌሎች ኮርሶች ተማሪዎች በአማርኛ የሚያከናዉኗቸዉ የፅሀፈት ስራዎች ንጽጽራዊ ጥናትen_US
dc.typeThesisen_US

Files

Original bundle
Now showing 1 - 1 of 1
No Thumbnail Available
Name:
ግርማ አውግቸው.pdf
Size:
27.17 MB
Format:
Adobe Portable Document Format
License bundle
Now showing 1 - 1 of 1
No Thumbnail Available
Name:
license.txt
Size:
1.71 KB
Format:
Plain Text
Description: