የክስታኔ ማኅበረሰብ የለቅሶ ሥርዓት ክዋኔ

dc.contributor.advisorዓለሙ ካሳዬ
dc.contributor.authorመሠረት ዓለሙ
dc.date.accessioned2026-08-14T11:03:13Z
dc.date.available2026-08-14T11:03:13Z
dc.date.issued2026-04-30
dc.description.abstractይህ ጥናታዊ ፅሁፍ የክስታኔ ማኅበረሰብ የለቅሶሥርዓት ክዋኔ በሚል የቀረበ ነዉ። የጥናቱ አላማ የክስታኔ ማህበረሰብ የለቅሶ ሥርዓተ ክዋኔን ማሳየትና የክዋኔዎችን ትዕምርት መተንተን ነዉ ።ጥናቱበምሥራቅጉራጌዞንየደቡብሶዶወረዳውስጥበሚገኙትስድስትቀበሌዎችላይያተኮረሲሆን፣የክዋኔንድፈሀሳብ፤የዓይነታዊጥናትሥነዘዴንናገላጭየመረጃመተንተኛዘዴንተከትሏል።መረጃዎቹ የተሰበሰቡት ተፈጥሮአዊ አዉድ ላይ በመገኘት ምልከታ በማድረግና ስለ ማህበረሰቡ ባህል ጥልቅ መረጃ አላቸዉ ተብለዉ ከታመነባቸዉ የሀገርሽማግሌዎችናየአካባቢውነዋሪዎችጋርቃለመጠይቅ በማካሄድ ነዉ።። በተገኘዉ መረጃ መሰረትምበክሰታኔማኅበረሰብ ሦስት የለቅሶሥነሥርዓት አይነቶች እንዳሉ፤ የለቅሶ ሥነሥርዓት ዓይነቶች ተብለው የተገለጹትም ልዩነት የሚታይባቸው በለቅሶ ግጥሞች መከወን አለመከወን፣ በግጥሞቹ ይዘት እና የለቅሶ ሥነሥርዓት ላይ በሚያዙ ቁሶችና አልባሳት መሆኑ ታዉቋል፡፡በፆታ ለሴትና ለወንድ፤ በዕድሜ ለሽማግሌ፣ለወጣት የሚገጠሙ ግጥሞች የተለያዩ እንደሆኑ ህፃናት ከሆኑ የተለየ የለቅሶ ክዋኔ ሆነ የለቅሶ ግጥም እንደማይደረግ ተመልክቷል። ጥናቱ የደረሰበት ሌላዉ ጉዳይ ማህበረሰቡ በቅድመሞትለሚከናወኑትተግባራት ቤተሰብ መንከባከብ፣ የታመመን በመጠየቅና በማሳከም፤ለኑዛዜሥርዓት ልዩ ትኩረት የሚሰጥ መሆኑን ነዉ። ይህ በቅድመ ሞት ላይ የሚያከናዉነዉ ቤተሰባዊና ማህበራዊ ተግባር ማህበረሰቡ ከቀብር በኋላ ለሚያከናዉነዉ (የሲቢታ ሴራ) ሥርዓት መሰጠትና አለመሰጠትን የሚወስን መሆኑን ማረጋገጥ ተችሏል። በክስታኔ ማህበረሰብ የለቅሶክዋኔውንበተመለከተ፣ወንዶችከዘራ፣ጡሩምባናመሳሪያይዘው፣ፈረስላይተቀምጠውናየነብርለምድለብሰውእየፎከሩ እንደሚያለቅሱ፤ ሴቶችበከበሮታጅበው፣ግጥምእየገጠሙ፣እጃቸዉን አንዴ ከደረት ወደዉጭ ሌላ ግዜ ደግሞ ከዉጭ ወደ ደረትእያርገበገቡ(እያቦሱ) ሟቹ የሠራቸወዉን ስራዎች፣ የተወለደበትን ዘርና ጎሳ እያወደሱ ሀዘናቸዉን እንደሚገልፁ በጥናቱተመልክቷል።የክስታኔ ማህበረሰብ ከቀብር መልስ እና በአስራሁለተኛውቀንየማብረድሥርዓት በማህበረሰቡ አጠራር (ዋብርድ) ሥርዓት እንዳለናሀዘንተኛመሆናቸዉንበተለያየመንገድእንደሚገልፁበተለይምባል የሞተባትሴትከአንድ እስከ ሁለት ዓመትድረስሥጋሳትበላ፣ ቅባት ሳትቀባ መሬትወይም ምድጃ (ገርገት)ተንተርሳእየተኛችእንድትቆይየሚያስገድድ ጥልቅ የሀዘን አገላለፅ እንደነበረና በአሁኑ ጊዜወደአንድዓመትዝቅ ማለቱን የተገኘው መረጃ ያሳያል። በማህበረሰቡ የለቅሶ ስርዓት ላይ ለውጦች ቢኖሩምየሲቢታሤራ፣የቁምለቅሶእናየማብረድሥርዓቶችመዝለቃቸውንናየለቅሶስርዓቱከሃዘን ባለፈ የሟችንማንነትየሚዘክርበትናቤተሰባዊና ማህበራዊትስስርየሚያጠናክርበት ትዉልድን በመልካም ምግባር እንዲቀረፅ የሚያደርግበት መሆኑ ታዉቋል።
dc.identifier.urihttps://etd.aau.edu.et/handle/123456789/8870
dc.language.isoam
dc.publisherAddis Ababa University
dc.subjectየለቅሶሥርዓት ክዋኔ በሚል የቀረበ ነዉ።
dc.titleየክስታኔ ማኅበረሰብ የለቅሶ ሥርዓት ክዋኔ
dc.typeThesis

Files

Original bundle
Now showing 1 - 1 of 1
No Thumbnail Available
Name:
መሠረት_ዓለሙ_2026_ETD.pdf
Size:
542.6 KB
Format:
Adobe Portable Document Format
License bundle
Now showing 1 - 1 of 1
No Thumbnail Available
Name:
license.txt
Size:
1.71 KB
Format:
Item-specific license agreed to upon submission
Description: