የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሰዋስውን ከዝርዝር ወደ ጥቅል እና ከጥቅል ወደ ዝርዝር ዘዴዎችን ተጠቅሞ ማስተማር የተማሪዎችን የሰዋስው እውቀትና ሰዋስውን የመማር ፍላጎት በማጎልበት ረገድ ያለው ሚና፤ በሻምቡ አብሼ ገርባ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ9ኛ ክፍል ተተኳሪነት
dc.contributor.advisor | ጌታቸው እንዳላማው (ዶ/ር) | |
dc.contributor.author | ሱሴ ተሻለ | |
dc.date.accessioned | 2023-12-21T12:17:56Z | |
dc.date.available | 2023-12-21T12:17:56Z | |
dc.date.issued | 2023-09 | |
dc.description.abstract | የዚህ ጥናት አቢይ ዓላማ ከዝርዝር ወደ አጠቃላይና ከአጠቃላይ ወደ ዝርዝር አቀራረብ ተጠቅሞ ሰዋስው ማስተማር በተማሪዎች የሰዋስው እውቀትና ሰዋስው የመማር ፍላጎት ላይ የሚኖረውን ሚና መመርመር ነው፡፡ የጥናቱ ተተኳሪዎች በሻምቡ ከተማ አስተዳደር በአብሼ ገርባ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2015 ዓ.ም. ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ከሚገኙ 513 ተማሪዎች 30 ተማሪዎች በእድል ሰጭ ንሞና ዘዴ የተመረጡ ናቸው፡፡ ጥናቱ ቅድመ ፍትነታዊ በመሆኑ የተማሪዎቹን የሰዋስው ችልታና ሰዋስው የመማር ፌላጎት ለማወቅ ቅድመ ትምህርት ፈተና እንዲፈተኑና የቅድመ ትምህርት ፍላጎታቸውን ለማወቅ ደግሞ የጽሁፍ መጠይቅ እንድሞሉ ተደርጓል፡፡ በመቀጠል የጥናቱን ዓላማ ከግብ ያደርሳል ተብሎ የተዘጋጀውን መጽሐፍ ለስድስት ሳምንት በሳምንት ሁለት ጊዜ ከፈረቃቸው ውጭ እንዲማሩ ተደርጓል፡፡ ከዚያም የጥናቱ ተሳታፉዎች ያመጡትን ለውጥ ለመለካት የድህረ ትምህርት ፈተና እንዲፈተኑና የድህረ ትምህርት የሰዋስው ፍላጎት የጽሁፍ መጠይቅ እንዲሞለሉተደርጓል፡፡ ለጥናቱ መረጃ ያስገኛሉ ተብለው በተግባር ላይ የዋሉት የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያዎች ፈተናና የፅሁፍ መጠይቅ ሲሆኑ በነዚህ ዘዴዎች አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች ተሰብስበዋል፡፡ የተሰበሰቡት መረጃዎች በዳግሞ ልኬት ናሙና ቲ-ቴስት ተተንትነዋል፡፡ በውጤት ትንተናው መሰረት የድህረ ሙከራ አማካይ ውጤት(30.77) ከቅድመ ሙከራ አማካይ ውጤት (23.53) በጉልህ በልጦ ተገኝቷል፡፡ ይህም ከዝርዝር ወደ አጠቃላይና ከአጠቃላይ ወደ ዝርዝር አቀራረብ ተጠቅሞ ሰዋስውን ማስተማር የተማሪዎችን ሰዋስው ዕውቀት እንደሚያጎለብት አመላክቷል፡፡ የድህረ ትምህርት ፍላጎት አማካይ ውጤት(42.4) ከቅድመ ትምህርት ፌላጎት አማካይ ውጤት(37.05) በልጦ ታይቷል፡፡ ይህም ዘዴዎቹን ተጠቅሞ ሰዋስውን ማስተማር በተማሪዎች ሰዋስው የመማር ፍላጎት ላይ ለውጥ እንዳመጣ ያሳያል፡፡ በመሆኑም በአማርኛ ቋንቋ ሰዋስው በማስተማር ከዝርዝር ወደ አጠቃላይና ከአጠቃላይ ወደ ዝርዝር አቀራረብ ተጠቅሞ የተማሪዎችን የሰዋስው ዕውቀትና ሰዋስው የመማር ፍላጎት በማጎልበት ረገድ የድህረ ትምህርት ፍላጎት ተመራጭ እንደሆነ አጥኚዋ ጠቁማለች፡፡ | |
dc.identifier.uri | http://etd.aau.edu.et/handle/123456789/1136 | |
dc.language.iso | am | |
dc.publisher | አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ | |
dc.subject | የሰዋስው እውቀት : ሰዋስው የመማር ፍላጎት | |
dc.title | የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሰዋስውን ከዝርዝር ወደ ጥቅል እና ከጥቅል ወደ ዝርዝር ዘዴዎችን ተጠቅሞ ማስተማር የተማሪዎችን የሰዋስው እውቀትና ሰዋስውን የመማር ፍላጎት በማጎልበት ረገድ ያለው ሚና፤ በሻምቡ አብሼ ገርባ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ9ኛ ክፍል ተተኳሪነት | |
dc.type | Thesis |