በደቡብ ምዕራብ ክልል የ8ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መፅሀፍ የቃላት አመራረጥ፣ አደረጃጀትና አቀራረብ ትንተና

No Thumbnail Available

Date

2023-09

Journal Title

Journal ISSN

Volume Title

Publisher

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ

Abstract

የዚህ ጥናት ዋነኛ አላማ በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ሕዝብ ክልል መንግስት ትምህርት ቢሮ በ2015 ዓመተ ምህረት ለ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ታስቦ በተዘጋጀው አማርኛ እንደ አፍ መፍቻ ቋንቋ መማሪያ መፅሀፍ ውስጥ የተካተቱ የቃላት ትምህርት ይዘት አመራረጥ አደረጃጀትና አቀራረብ መገምገም ነው። እንዲሁም መማሪያመፅሀፉ መርሀትምህርቱን መሰረት አድርጎ ስለሚዘጋጅ የቃላት ምህርቶችን መርጦና አደራጅቶ ለማቅረብ የራሱ አስተዋፅኦ ስለሚኖረው የሁለቱን ተጣጥሞሽ ይቃኛል። ጥናቱን ከግብ ለማድረስ የተለያዩ ምሁራን ስለቃላት ትምህርት ይዘት አመራረጥ አደረጀጀትና አቀራረብ ባነሷቸው ንድፍ ሀሳባዊ መርሆች ላይ በመመርኮዝ ጥናት ተካሄዷል። በጥናቱም ተተኳሪው መፅሀፍና ለክፍል ደረጃውየተዘጋጀው መርሀትምህርት በመረጃ ምንጭነት አገልግለዋል። ከነዚህ ሁለት ሰነዶች መረጃውን ለመሰብሰብ የሰነድ ፍተሻ በጥቅምላይ ውሏል። ከሰነድ ምርመራው የተገኙ መረጃዎችን በቁጥርና በመቶኛ በማስቀመጥ በገለፃ ስልት ተተንትነዋል።ጥናቱ ቅይጥ የትንተና ዘዴን ተከትሎ የተሰራ በመሆኑ በዋናነት አይነታዊ ዘዴን በአጋዥነት ደግሞ መጠናዊ የአጠናን ዘዴን ለትንታኔ ተጠቅሟል።በጥናቱ የተገኘው ውጤት እንደሚያመለክተው በመማሪያ መፅሀፉ ውስጥ ለቃላት ትምህርት ሰፊ ሽፋን ትኩረት ተሰጥቷል። ይሁን እንጂ የቃላትመረጣው የተከናወነው የመስኩ ምሁራን ለዚህ ተግባር እንዲውሉ ከሰነዘሯቸው መስፈርቶች አንዱን ብቻ በመጠቀም ነው።እሱም አንድ ቃል ሰፊ አገልግሎት ሽፋንና ስርጭት ባይኖረውም እኳን ለቋንቋ ማስተማሪያነት በሚቀርበው ምንባብ ውስጥ የተለየ አስፈላጊነት ይዞ ሲገኝ የሚመረጥበት በቅርበት የመገኘት መስፈርትን የተመለከተ ነው። ሌሎቹ የቃላት ድግግሞሽ መጠን የፍቺ ሽፋን ተስተማሪነትና የተማሪዎች ፍላጎት ከግምት በማስገባት መምረጥ የሚሉት ትኩረት አልተደረገባቸውም፡፡ አደረጃጀትን በተመለከተ የቃላት ትምህርቶቹ የመማር ሂደቱ በጠበቀ መልኩ ከቀላል ወደ ከባድ እንደተደራጁ ጥናቱ ያመላክታል። ከአንድ ቃል ጋር አብረው ሊሰለፉ የሚችሉ ቃላዊ ሀረጎች ማለትም ጥምር ቃላትን፥ በጥመራ የሚፈጠሩ ፈሊጦችን የመሸጋገሪያ ቃላትንመርጦና አደራጅቶ ለትምህርትነት ከማቅረብ አንፃር ትኩረት እንደተሰጠባቸው በጥናቱ ተረጋግጧል። ከፍቺ ተዛምዶ አንፃር የቃላት የከታች ተከታች ግንኙነትን ለማስተማር የቀረቡተግባራት በመማሪያ መፅሀፉ አልተካተቱም። ቃላትን በአውድ አስደግፎ ማቅረብና በፍቺ ተዛምዷቸው ማቅረብ ሰፊ ሽፋን ተሰጥቷቸው ቀርበዋል። የቃላትን ትምህርት ከማድመጥና ከመናገር ክልሎች ጋር አጣምሮ ከማቅረብ አንፃር ውስንነት ታይቷል። ተማሪዎች የመዝገበ ቃላትን አጠቃቀም ጥበብ እንዲያውቁ የሚያግዙ ተግባራት እንደተካተቱ የጥናቱ ውጤት ያሳያል። መማሪያ መፅሀፉና ለክፍል ደረጃው የተዘጋጀው መርሀ ትምህርት አብዛኛው ቦታላይ ተጣጥሞሽ ያላቸው ሲሆን በተወሰነ መልኩ የማይጣጣሙበት ሁኔታ እንዳለ በጥናቱ ተጠቁሟል። በመጨረሻም ከጥናቱ ግኝት ጋር በተያያዘ መልኩ ከተጠቀሱት አስተያየቶች መካከል ለምሳሌ የቃላት መረጣ ሲካሄድ በተቻለመጠን ቋንቋንለጠቅላላ አላማ ለማስተማርታስቦ ለሚነደፍ መርሀግብር እንዲውል በመስኩምሁራን ለተሰነዘሩት የቃላትመምረጫ መስፈርቶች ተገቢትኩረት ቢሰጥ፥እንዲሁም ለትምህርት የሚቀርቡየቃላት ተግባራት የማስተማራያ ምንባቦች ውስጥ ብቻ ባይወሰኑ፥ ከምንባቡ ውጪም ተገቢየሆነ አውድ ተፈጥሮላቸው ቢቀርቡ፥ የቃላት ትምህርት አደረጃጀትን በተመለከተ ደግሞ ከሚያነሱት ርዕሰጉዳይ አንፃር ቃላትን ማደራጀት የሚለው መስፈርት የተሰጠው ሽፋን አነስተኛ በመሆኑ ሚዛናዊ አድርጎ ለማደራጀት ቢሞከርና የመሳሰሉትን አስተያየቶች በመስጠት ተጠናቋል።

Description

Keywords

ደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ፡አፍ መፍቻ ቋንቋ

Citation