የገፀ-ባህርያት አሳሳል በከርታታው ልቦለድ
dc.contributor.advisor | ሰላማዊት መካ | |
dc.contributor.author | ሳሙኤል ደመቀ | |
dc.date.accessioned | 2025-07-16T08:56:55Z | |
dc.date.available | 2025-07-16T08:56:55Z | |
dc.date.issued | 2001-06 | |
dc.description.abstract | ይህ ጥናት “የገፀ-ባህርያት አሳሳል በከርታታው ልቦለድ” በሚል ርዕስ፣ በ1999 ዓ.ም በደራሲ ባህሩ ዘርጋው የታተመውን ከርታታው በጥናቱ ውስጥ የደራሲው የገፀ-ባህርያት አሳሳል እንዴት እንደሆነ ከመታየቱ በፊት ከዚህ ጥናት አስቀድሞ በገፀ-ባህርያት አሳሳል ላይ የተሰሩ የተዛማጅ ፅሁፎች ቅኝት ተደርጓል፡፡ ከዚያም ስለገፀ-ባህርያት አሳሳል ስልት ትወራዊ ዳራ ተሰጥቷል፡፡ ረጅም ልቦለድ ይመለከታል፡፡የጥናቱ መነሻ ደራሲው ለመጀመሪያ ጊዜ ባሳተሙት በዚህ ልቦለድ ውስጥ ያሉ ገፀ-ባህርያትን እንዴት እንደሳሉ ለመተንተን እና በገፀ-ባህርያት አሳሳል ወቅት ያሳዩት ድክመትም ሆነ ጥንካሬን ለመገምገም ነው፡፡ ከዚያም በተጨማሪ ደራሲው አዲስ የገፀ-ባህርያት አሳሳል ስልት መጠቀማቸውን ለማሳየት ነው፡፡በድርሰቱ ውስጥ ገፀባ-ህርያቱን ለመሳል በአንደኛ መደብ የትረካ አንጻር (እኔ ባይ) ተራኪ በስፋት ይታያል፡፡በዚህ ልቦለድ ውስጥ ደራሲው ትኩረት የሰጡበትና ጠንከር ብሎ የታየው ጉዳይ የገፀ-ባህርያት ውስጣዊ ባህሪ ላይ ሲሆን በአካላዊ ገለፃው ረገድ ደከም ብሎ ይታያል፡፡ ከንዑስ ገፀባ-ህርያት ይልቅ በዋና ገፀባ-ህርያት ላይ የተጠቀሙት አካላዊ ገለፃ ይህ ነው የሚባል አይደልም፡፡በልቦለዱ የታየው የገፀባ-ህርያት አሳሳል ስልት እንብዛም ሆኖ ተገኝቷል፡፡ አብዛኛዎቹ ገፀባ-ህርያት ውጫዊ መልካቸውና ውስጣዊ ባህሪያቸው ተመሳሳይ መሆኑ ገፀ-ባህርያቱን ወደ ግጭት እንዳይገቡ ስላደረጋቸው የገሀዱ አለም ነፀብራቅ ይሆኑ ይሆን? የሚል ጥያቄ ያስነሳል፡፡ አንዳንዶቹ ገፀባ-ህርያት ወጥነት የጐደላቸውና ኢተአማኒ ናቸው፡፡ በመጽሐፉ የታየው ሙት መንፈስን የወከለው ገፀ-ባህሪ ለአገራችን አንባቢያን አዲስ በመሆኑ ስለሙት መንፈስ በመጠኑም እንዲያውቅ በመደረጉ ይደነቃል፡፡በመጨረሻም ይህ ጥናት በጥናቱ ማጠቃለያ ስር የዚህን ልቦለድ ድክመትና ጥንካሬ በማውጣት ለማሳየት ሞክሯል፡፡ ገፀ-ባህርያቱ በአብዛኛው ተመሳሳይ አካላዊ መልክና ሕኒናዊ ባህሪ መያዛቸው ልቦለዱን ከድርሰት አፃፃፍ አንፃር ደካማ ሲያደርገው፤ በመጽሐፉ የተሳሉት ብዙዎቹ ገፀ-ባህርያት ቆራጥነታቸውና የአላማ ጽናታቸው እስከ ታሪኩ መጨረሻ መዝለቁ ከዘላቂነት አንፃር መጽሐፉ ያሳየው ጥንካሬ ነው፡፡ | |
dc.identifier.uri | https://etd.aau.edu.et/handle/123456789/5645 | |
dc.language.iso | am | |
dc.publisher | አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ | |
dc.subject | ከርታታው በጥናቱ ውስጥ የደራሲው የገፀ-ባህርያት አሳሳል እንዴት እንደሆነ ከመታየቱ በፊት ከዚህ ጥናት አስቀድሞ በገፀ-ባህርያት አሳሳል ላይ የተሰሩ የተዛማጅ ፅሁፎች ቅኝት ተደርጓል፡፡ ከዚያም ስለገፀ-ባህርያት አሳሳል ስልት ትወራዊ ዳራ ተሰጥቷል፡፡ ረጅም ልቦለድ ይመለከታል፡፡የጥናቱ | |
dc.title | የገፀ-ባህርያት አሳሳል በከርታታው ልቦለድ | |
dc.type | Thesis |