የወላይትኛ አፈ-ፈት ተማሪዎች በአማርኛ ድርሰት ሲጽፉ የሚፈፅሟቸው ዋና ዋና የስህተት ዓይነቶች እና የስህተት ምንጮች ትንተና፡ በ10ኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት

No Thumbnail Available

Date

2023-09

Journal Title

Journal ISSN

Volume Title

Publisher

Addis Ababa University

Abstract

የዚህ ጥናት አብይ ዓላማ በወላይትኛ ቋንቋ አፋቸውን የፈቱ ተማሪዎች በአማርኛ ድርሰት ሲጽፉ የሚፈጽሟቸው ስህተቶችና የስህተት ምንጮችን በመለየት ስህተቶችን መተንተን ነው፡፡ ጥናቱም አይነታዊና መጠናዊ የምርምር ዘዴን የተከተለ ሲሆን፣ ለአቀራራቡ ገላጭ ሰልት ተግባራዊ ተደርጓል፡፡ መጠናዊ የምርምር ዘዴ ተግባራዊ የተደረገው በተማሪዎች ድርሰት ውስጥ የታዩ የስህተቶቹን ብዛት እና የድግግሞሽ መጠን ለመለየትና ለመተንተን ነው፡፡ የጥናቱ ተሳታፊዎች በ2015 ዓ.ም. በወላይታ ዞን በዳሞት ወይዴ ወረዳ በዴሳ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ይማሩ የነበሩ በወላይትኛ አፈ-ፈት የሆኑ የ10ኛ ክፍል 55 ተማሪዎች ናቸው፡፡ የጥናቱ መረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያዎች በክፍል ውስጥ በተማሪዎች የተጻፈ ድርሰት፣ የሰነድ ፍተሻ፣ የጽሁፍ መጠይቅ እና ቃለመጠይቅ ሲሆኑ፣ መረጃዎች በገላጭ ስልት ተተንትነዋል፡፡ የጥናቱ ውጤት በተማሪዎች ድርሰት ውስጥ ከታዩ ከቋንቋ አጠቃቀም፣ ከቋንቋ አወቃቀር፣ ከስርዓተ ነጥብ አጠቃቀም እና ስርዝ ድልዝ ስህተቶች ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ የስህተት ምንጮች የአፍ መፍቻ ቋንቋ ጣልቃ ገብነት፣ የውስጠ-ቋንቋ ተጽዕኖ፣ የመማሪያ ክፍል ውስጥ አውድ (የመማር ማስተማር ሂደትና የማስተማሪያ መሳሪያዎች) እና ማህበራዊና ስነልቦናዊ ተጽዕኖ መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡ ስለሆነም ባለድርሻ አካላት ሁሉ ከጥናቱ ውጤት በመነሳት በአማርኛ ቋንቋ ኢ-አፈ-ፈት የሆኑ ተማሪዎች የተለያዩ የክፍል ውስጥ ተግባራትን በማዘጋጀት ማስተማር ይጠይቃል፡፡

Description

Keywords

በወላይትኛ ቋንቋ አፋቸውን የፈቱ ድርሰት ሲጽፉ

Citation