የአማርኛ ቋንቋ መምህራን የመፃፍ ክሂል ማስተማሪያ ዘዴዎች አተገባበር /በጋሞ ዞን በአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ በ9ኛ እና በ10ኛ ክፍል/

dc.contributor.advisorግርማ ገብሬ ዶ/ር
dc.contributor.authorዘሪሁን አሰፋ
dc.date.accessioned2024-09-26T06:14:34Z
dc.date.available2024-09-26T06:14:34Z
dc.date.issued2024-01
dc.description.abstractየዚህ ጥናት ዋና ዓላማ በጋሞ ዞን በአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የዘጠነኛ እና የአስረኛ ክፍሎች የአማርኛ ቋንቋ መምህራን የመፃፍ ክሂል ማስተማሪያ ዘዴቾን አተገባበርን የሚመለከት ነው፡፡ ይህን ዓላማ ከግብ ለማድረስ የቋንቋ ምሁራን ያቀረቧቸውን ንድፈ ሀሳቦች መሰረት በመድረግ በጥናቱ የተሳተፉት የአማርኛ ቋንቋ መምህራን የመጻፍ ክሂል ማስተማሪያ ዘዴዎች አተገባበር እንዲከወን ተደርጓል፡፡ ጥናቱን ከዳር ለማድረስ ምልከታ ጥቅም ላይ የዋለ ሲሆን በተቸማሪ የጽሁፍ መጠይቆችን በመምህራንና በተማሪዎች በመስሞላት መምህራን ጽህፈትን ስለሚያስተምሩበት የማስተማሪያ ዘዴ የሚጠቅሙ መረጃዎች ተሰብስበዋል፡፡ መረጃዎቹ የአይነታዊ ምርምር ዘዴን በመጠቀም በገላጭ ስልት ተተንትነዋ፡፡ ከጥናቱ የተገኘው ውጤት እንደሚያመለክተው መምህራን ተማሪዎችን በተግባራዊ ሂደት እንዲማሩ ከማመቻቸት ይልቅ በገለጻ የሚያስተምሩ መሆናቸውን መረጃዎች አመልክተዋል፡፡ በክፍል ውስጥ ተግባራዊ የሚደረገው የማስተማሪያ ዘዴ የጽህፈት ተግባቦትን የሚያዳብር እና ተማሪዎችን የሚያሳትፍ አይደለም፡፡ ተማሪዎች የተለያዩ ለጽህፈት ክሂል ማዳበር የሚረዱ ሂደቶችን አውቀው እየተገበሩ እንዲሻሻሉ የሚደረግ ጥረት ደካማ ነው፡፡ ተማሪዎች እርስ በርስ እንዲመማሩና እንዲተራረሙ የሚተገበረው ተግባር ውስንነት አለበት፡፡ በአባዛኛው መምህራን ትኩረት ሰጥተው የሚተገብሩት ተማሪው በተሰጠው ርዕስ ላይ ጽፎ ባቀረበው ውጤት ላይ ነው፡፡ ለችግሩ መኖር በዋናነት የተጠቀሰው መንስኤ መምህራን ለጽህፈት ትምህርት አቀራረብ ያላቸው ግንዛቤ አነስተኛ በመሆኑ ነው፡፡ በአጠቃላይ ለችሮቹ መፍተሔ ሊሆን ይችላል ተብሎ የሚገመተው መምህራን ከአዳዲስ የማስተማሪያ ዘዴዎች ጋር እንዲተዋወቁ ስልጠና መስጠት ተጦቁሟል፡፡
dc.identifier.urihttps://etd.aau.edu.et/handle/123456789/3478
dc.language.isoam
dc.publisherአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ
dc.titleየአማርኛ ቋንቋ መምህራን የመፃፍ ክሂል ማስተማሪያ ዘዴዎች አተገባበር /በጋሞ ዞን በአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ በ9ኛ እና በ10ኛ ክፍል/
dc.typeThesis

Files

Original bundle
Now showing 1 - 1 of 1
No Thumbnail Available
Name:
ዘሪሁን አሰፋ.pdf
Size:
710.57 KB
Format:
Adobe Portable Document Format
License bundle
Now showing 1 - 1 of 1
No Thumbnail Available
Name:
license.txt
Size:
1.71 KB
Format:
Item-specific license agreed to upon submission
Description: