በኦሮምኛ ቋንቋ አፋቸውን የፈቱ የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት የቃላት መማር ብልሃቶች አጠቃቀም ፍተሻ፤ በአዋሮ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተተኳሪነት
No Thumbnail Available
Date
2023-10
Authors
Journal Title
Journal ISSN
Volume Title
Publisher
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ
Abstract
ጥናቱ በኦሮምኛ ቋንቋ አፋቸውን የፈቱ የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች የአማርኛን ቃላት ሲማሩ የሚጠቀሙባቸውን ቃላትን የመማር ብልሃቶች የሚፈትሽ ነው፡፡ በአምቦ ከተማ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ከሚሰጥባቸው አምስት የመንግስት ትምህርት ቤቶች መካከል በቀላል የእጣ ናሙና ዘዴ በተመረጠው የአዋሮ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ9ኛ ክፍል የሚማሩ በኦሮምኛ ቋንቋ አፋቸውን የፈቱ 60 ተማሪዎችን በተመጣጣኝ ናሙና ዘዴ በመውሰድ በዓይነታዊ የምርምር ዘዴ ያካሄደ ገላጭ ጥናት ነው፡፡ በዚህም መሰረት የሁለተኛን ቋንቋ ቃላት በቀላሉ ለመማር በተለያየ መንገድ እገዛ በሚያደርጉ ( የትውስታ ፣ አእምሮታዊ፣ አካካሽ ልዕለ አዕምሮታዊ ፣ ስሜት ነኪ ቁጥጥር እና ማህበራዊ ) ብልሃቶች ስር በተካተቱ ዝርዝር ብልሃቶች ላይ በማተኮር ተጠኚ ተማሪዎች የአማርኛ ቋንቋ ቃላትን ሲማሩ የተጠቀሱትን የመማር ብልሃቶች ምን ያህል እንደሚገለገሉባቸው ለመፈተሸ ተሞክሯል፡፡ ለጥናቱ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች በጽሑፍ መጠይቅና በቃለ መጠይቅ የተሰበሰቡ ሲሆን ፣ በጽሑፍ አማካይነት የተገኙ መረጃዎችም በስድስት ንዑሳን የመማር ብልሃቶች ስር በሰንጠረዥ ተደራጅተው ፣ በቁጥርና በመቶኛ ተጠቃልለው እንዲታዩ በማድረግ በቃለ መጠይቅ ከተገኙ መረጃዎች ጋር እየተደጋገፉ ተተንትነዋል፡፡ በሁለቱም የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያዎች በተገኙ መረጃዎች ትንተና ውጤት መሰረትም፣ ተማሪዎቹ የአማርኛ ቃላትን የሚማሩበት መንገድ የሁለተኛን ቋንቋ ቃላት በቀላሉ ለመማር በተለያየ መንገድ ዕገዛ የሚያደርጉ ቃላትን የመማር ብልሃቶች በብቃት በመጠቀም ላይ የተመሰረተ ሆኖ አልተገኘም ፡፡ አብዛኞቹ ተማሪዎች የታላሚውን ቋንቋ አዳዲስ ቃላት በአእምሮአቸው መዝግበው የረጅም ጊዜ ትውስታ ለመፍጠር የሚያግዟቸውን የትውስታ ብልሃቶች ፣በትምህርቱ ሂደት የሚሰማቸውን የፍርሃት፣ የጭንቀት ፣ አሉታዊ አመለካከትና ዝንባሌ ለመቆጣጠር የሚረዷቸውን ስሜት ነኪ ቁጥጥር ብልሃቶችን፣ የቃላት ዕውቀታቸውን ለማዳበር በሚል ዓላማ ከክፍል ጓደኞቻቸው ጋር እየተረዳዱ ፣ መምህሮቻቸውን እየጠየቁ የመማር ፣ ማህበራዊ ብልሃቶችንና ለቃላት ትምህርት የክንውን ዕቅድ በማዘጋጀት፣ ዓላማና ግብ በመንደፍ ፣ ስህተታቸውን በራሳቸው በመለየትና በመገምገም እንዲማሩ የሚያግዟቸውን ልዕለ አዕምሮታዊ ብልሃቶችን አብዛኛዎቹ ተማሪዎች አልፎ አልፎ እንደሚገለገሉባቸው የተገኘው መረጃ ትንተና ውጤት ያመለክታል፡፡
Description
Keywords
በኦሮምኛ ቋንቋ አፋቸውን የፈቱ፡ ቃላትን የመማር ብልሃቶች