በትግርኛ ቋንቋ አፍቸውን የፈቱ የስምንተኛ እና የአስረኛ ክፍል ተማሪዎች በአማርኛ ንባብ ጊዜ የንባብ ብልሃት አጠቃቀም እና የመምህራን ግንዛቤ ተጣጥም ፍተሻ- በአክሱም ከተማ እንደኛእና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መነሻነት

No Thumbnail Available

Date

2000-01

Journal Title

Journal ISSN

Volume Title

Publisher

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

Abstract

ጥናቱ በቋንቋ ችሎታቸው በከፍተኛ፤በመካከለኛ እና በዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ በትግርኛ ቋንቋ አፍቸውን የፈትቱ የስምንተኛ ክፍል ተተኳሪ ተማሪዎች የንባብ ብልሃቶችን በብዛት በመጠቀም ረገድ በቋንቋ ችሎታቸው ካገኙት ደረጃ ጋር መጣጣም አለመጣጣሙን የሚመረምር አና የተተኳሪ ተማሪዎች የአማርኛ መምህራን የንባብ ብልሃት ግንዛቤ ከተተኳሪ ተማሪዎቹ የንባብ ብልሃት አጠቃቀም ጋር መጣጣም አለመጣጣሙን የሚፈትሽ ነው፡፡ በዚህ መሠረት ተማሪዎቹን በኢላማ ናሙና በአማካይ የአማርኛ ፈተና ውጤታቸው መሠረት ከየክፍል ደረጃው ስድስት ተማሪዎች የተመረጡ ሲሆን፤ መምህራኑም ተማሪዎቹ በሚማሩባቸው መማሪያ ክፍሎች የሚያስተምሩ እንዲሆኑ በማድረግ በኢላማ ናሙና ተመርጠዋል፡፡ የተማሪዎቹን የንባብ ብልሃት አጠቃቀም ለማጥናትም የተራኪ እና የአስረጅ ድርሰት ምንባባት በመምረጥ እና የአንብቦ መረዳት ጥያቄዎችን ማዘጋጀት አሰፈላጊ ሆኗል ፡፡ ከዚያም ምንባቡን እያነበቡ የአንብቦ መረዳት ጥያቄዎቹን ሲመልሱ የሚጠቀሙባቸውን የንባብ ብልሃቶችን ከአእምሮአዊ የማሰብ ሂደታቸው (introspection) ቃላዊ መረጃ እንዲያቀብሉ ተደርጓል፡፡ በዚህ መሠረት በተደረገው ምልከታ በቪድዮ ካሜራ እና በመቅረፀ ድምፅ ተቀርፀዋል፡፡ የተጠቀሙባቸውን የንባብ ብልሃቶችን ለመተነተንም የSarig (1987) የንባብ ብልሃት አከፍፈል በምዴልነት ተወስዷል፡፡በምልከታ የተገኙትን መረጃዎች ለማመሳከርም የፅሑፍ መጠይቅ አና ቃለመጠይቅ ግልጋሎት ላይ ውለዋል፡፡ የመምህራኑን የንባብ ብልሃት ግንዛቤ ለመፈተሸ ደግም ቃለ መጠይቅ በዋነኛነት የፅሑፍ መጠይቅ ደግም በደጋፊነት ሥራ ላይ ውለዋል፡፡

Description

Keywords

Citation