የቤተሰብ ዳራ የአንብቦ መረዳት ችሎታን የመተንበይ ድርሻ፤ በአምስተኛና በሰባተኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት

No Thumbnail Available

Date

2010-06

Journal Title

Journal ISSN

Volume Title

Publisher

Addis Ababa University

Abstract

የዚህ ጥናት ዋና አላማ የቤተሰብ ዳራ የአንብቦ መረዳት ችሎታን የመተንበይ ድርሻውን መለየት ነው፡፡ ተሳታፊዎች በዶና በርበር የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2010 ዓ.ም ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙ በዕጣ ንሞና የተመረጡ 151 የአምስተኛና 170 የሰባተኛ ከፍል ተማሪዎች ናቸው፡፡ ከተሳታፊዎች መረጃ የተሰበሰበው በሶስት የተለያዩ የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴዎች ነው፡፡ እነሱም የጽሁፍ መጠይቅ፣ ፈተናና የቡድን ውይይት ናቸው፡፡ ፈተናው አንብቦ መረዳት ችሎታን፣ መጠይቁ የቤተሰብ ዳራን ለመለካት ሲያገለግል የቡድን ውይይቱ ደግሞ ተጨማሪ የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴ በመሆን አገልግሏል፡፡ የተሰበሰቡት መረጃዎች አስተማማኝነት፣ ተገቢነትና የውጤት ስርጭት ወጥነት ተሰልቶ ከተረጋገጠ በኋላ ሁሉም መረጃዎች በተንባይና ገላጭ ስታትስቲክሶች አማካኝነት ተተንትነው ተብራርተዋል፡፡ የተገኘው መረጃ የፓራሜትሪያዊ መፈተሻ ዘዴዎችን ለመጠቀም የሚያስችል በመሆኑ ተግባራዊ የተደረጉት የመተንተኛ ዘዴዎች የህብረ ድህረት ትንተናና የነጻ ናሙና ቲቴስት ናቸው፡፡ በትንተናው መሰረት የቤተሰብ ዳራ የአንብቦ መረዳት ችሎታን ጉልህ ተንባይ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ከቤተሰብ ዳራ ዝርዝር ተላውጦዎች የአንብቦ መረዳት ችሎታን በከፍተኛ ደረጃ የተነበዩት የቤተሰብ የኢኮኖሚ ደረጃና የቤተሰብ የትምህርት ደረጃ ናቸው፡፡ የቤተሰብ የኢኮኖሚ ደረጃ መለኪያ የሆኑት ወርሀዊ ገቢና ß= 0.5ና ገቢ ከአካባቢ ጋር ሲነጻጸር ß= 0.119 የቤተሰብ የትምህርት ደረጃ ß= 0.382 ከፍተኛ የመደበኛ ቤታ ዋጋ በማምጣት ከሌሎች ተላውዎች በተሻለ ጉልህ ተንባይ ሆነዋል፡፡ ይህ ውጤት በሁለቱም የክፍል ደረጃ ተቀራራቢ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በተጨማሪነት የታየው ሌላው ጥያቄ የአንብቦ መረዳት ችሎታ በጾታ ልዩነት እንዳለው መቃኘት ሲሆን የወንዶች አማካኝ ችሎታ ከሴቶች የተሻለ ሆኖ ቢገኝም በሁለቱ መካከል ያለው ልዩነት ጉልህ እንዳልሆነ በትንተናው ተረጋግጧል፡፡ የአምስተኛ ክፍል ተማሪዎች ወንዶች 22.51 ሲሆን የሴቶቹ 21. 63 የሰባተኛ ክፍል ወንዶች 17.74 የሴቶች 17.13 ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ከዚህ ውጤት በመነሳትም በትምህርት ቤት ውስጥ የኢኮኖሚ ችግር ያለባቸውን ልጆች ድጋፍ ማድረግና ያልተማሩ ወላጆችን የተለያዩ የመሰረታዊ ትምህርት እንዲያገኙ ማድረግ የሚሉ የመፍትሄ ሀሳቦች ተሰጥተዋል፡፡ ለሴቶች የተለያዩ ድጋፎችን መስጠት የሚል ስነትምህርታዊ አንድምታ ተሰጥቷል፡፡ በተጨማሪም በረጅም ጊዜ የጥናት ስልት፣ ወላጆችንና መምህራንን ተሳታፊ በማድረግ፣ አጠቃላይ ከአንድ እስከ ስምንት የሚገኙ ተማሪዎችን በማካተት እንዲም በርካታ ናሙና ወስደው ማጥናት ይቻላል የሚሉ የምርምር ጥቆማዎችም ተሰጥተዋል፡፡

Description

Keywords

የቤተሰብ ዳራ የአንብቦ መረዳት ችሎታን የመተንበይ ድርሻውን መለየት ነው

Citation