በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ከርሰቲያን በአዲስ አበባ ሐገረ ሰብከት ውሰጥ በሚደረጉ ሰብከቶች ወቅት የሚነገሩ ቃላዊ ዝርው ተረኮች ጥናት

No Thumbnail Available

Date

2003-01

Journal Title

Journal ISSN

Volume Title

Publisher

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

Abstract

ቃላዊ ዝርው ተረኮች ለባህል ባለቤቶቹ (ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን) ያላችውን ፍይዳ ወይም ተግባር መመርመርና ከዋኔያቸውን የክዋኔ እውድን መቃኘት የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ ነው፡፡ በዚህ መሠረት የተረኮቹ ክዋኔ፤ የከዋኙና የታዳሚው ማንነትና መሰተጋብር፤ የክዋኔ እውድ፤ የአከዋወን ስልት ምን ይመሰላል ? ተረኮቹ በባህል ባለቤቶቹ ዘንድ ያላቸው ተግባር ምንድነው? እንዲሁም ተለይተው የሚታወቁበት ስያሜና የአመዳደብ ስርዓት አላቸው ወይ? ለሚሉት ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት ጥሪት ተደርጓል ፡፡ በውጤቱም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰብከት ስርዓት ወቅት የሚነገሩ ቃላዊ ዝራው ተረኮች በባህል ባለቤቶቹ ዘንድ ተለይተው የሚታወቁበት አንድ ወጥ ስያሜም ሆነ የአመዳደብ ተረኮቹ በባህል ባለቤቶቹ ዘንድ ያላችው ተግባር ምንድነው እንዲሁም ተሰይተው የሚታወቁበት ስያሜና የአመዳደብ ስርዓት አላቸው ወይ ለሚሉት ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት ጥረት ተደርጓል፡፡ በውጤቱም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በስብከት ስርዓት ወቅት የሚነገሩ ቃላዊ ዝርው ተረኮች በባህል ባለቤቶቹ ዘንድ ተለይተው የሚታወቁበት አንድ ወጥ ስያሜም ሆነ የአመዳደብ ስርዓት እንደሌላቸው ለማሳየት ተምክሯል፡፡ ይሁንና በተረኮቹ ክዋኔ ሂደት ታዳምያንና ከዋኞቹ ከሚፈዕሟቸዉ ልዩ ልዩ ተግባራትና በውስጠ ታዋቂነት ከሚያንፀባርቁት አመለካከት በመነሳት ተረኮቹን እውነተኛና ፈጠራዊ በሚሉ አበይት ምድቦች ለመክፈል ተምከሯል፡፡ በጥናቱ ሃደት ተራኪዎች በክዋኔ ላይ ልዩ ልዩ የአከዋወን ስልትን እንደሚከተሉ የታየ ሲሆን፤ ከትረካ መስመር መውጣት/ digression/;ድግግምሸ እና ወደረኛ ቅንብር ከስልቶቹ መካከል ተጠቃሸ እንደሆኑ በጥናቱ ተጠቁሟል፡፡ ጥናቱ በስብከት ስርዓት ወቅት የሚከወኑ ቃላዊ ዝርው ተረኮችን ከፎክሎር ተግባራዊ ጥናት /fuctionalist approaches/ አንዓር ትንታኔ ስጥቷል፡፡ በዚህ መሠረት ተረኮቹ የቤተ ክርስቲያኑን እሴት የማሰተማር፤ ምዕመናን ከቤተ ክርስቲያኑ የእሴት ስርዓት አፈንግጠው እንዳይወጥጡ የመቆጣጠርና የመግታት እንዲሁም ለምዕመናኑ ስነልቡናዊ እፎይታን የመስጠት ፍይዳ እንዳላቸው ለማሳየት ጥረት ተደርጓል፡፡ ከነዚህ ተግባራት ጎን ለጎን ዝርው ተረኮቹ ከሃይማኖታዊ ጉዳዮች ቅንብብ ዘልቀው በመውጣት በተራቹ ማህበረሰብ፤ ማህበራዊ ህይወት ዙሪያ የማሄስ ተግባርን እንደሚፈዕሙ ለመጠቆም ተምክሯል ፡፡

Description

Keywords

Citation