የድጋፍ ብልሃቶች በአንብቦ የመረዳት ችሎታ እና ግለመር ማንበብ ላይ ያላቸው ተፅዕኖ፤ በ7ኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት

No Thumbnail Available

Date

2016-10

Journal Title

Journal ISSN

Volume Title

Publisher

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

Abstract

የዚህ ጥናት ዓላማ የድጋፍ ብልሃቶች የተማሪዎችን በአማርኛ ቋንቋ አንብቦ የመረዳት ችሎታ እና ግለመር ማንበብ ላይ ያላቸውን ተፅዕኖ መፈተሸ ነበር፡፡ ጥናቱ በዓይነቱ ቅደምተከተላዊ ቅይጥ (በአመዛኙ መጠናዊ) ሲሆን ቅድመና ድህረ ትምህርት ባለቁጥጥር ቡድን ፍትነት መሰል ንድፍን የተከተለ ነው፡፡ በ2015 ዓ.ም በአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር፣ በጉለሌ ክፍለ ከተማ በአዲስተስፋ አንደኛ ደረጃ ትምህርትቤት የ7ኛ ክፍል ተማሪዎች ተሳትፈዋል፡፡ መረጃዎችን ለመሰብሰብም አንብቦ የመረዳት ችሎታ ፈተናና የግለመር ማንበብ መጠይቅ ጥቅም ላይ ውለዋል፡፡ ሌላው በአጋዥነት ድህረቡድን ተኮር ውይይት ተግባራዊ ሆኗል፡፡ እንዲሁም ሁለቱ ቡድኖች በተቀመጠላቸው የማስተማሪያ መንገድ መማራቸውን ለማረጋገጥ ሲባል ምልከታ ተካሂዷል፡፡ በቅድመ ፈተናና በቅድመ የጽሑፍ መጠይቅ የተገኙ ውጤቶች በጥንድና ነፃ ቲ-ትስቶች የትንተና ስልት እንዲሁም በድኅረ ፈተናና በድኅረ የጽሑፍ መጠይቅ የተገኙ ውጤቶች በጥንድ፣ ነፃ ቲ-ትስቶችና በአበር ልይይት ትንተና ስልቶች ተተንትነዋል፡፡ በተጨማሪም ከድህረቡድን ተኮር ውይይት የተገኙ አይነታዊ መረጃዎች በጭብጥ ትንተና ዘዴ ተተንትነዋል፡፡ ከትንተናው የተገኙት ውጤቶችም እንደሚያመለክቱት በቅድመፈተናና በቅድመየጽሑፍ መጠይቅ ቡድኖች ተመጣጣኝ አማካይ ውጤቶች ያስመዘገቡ ሲሆን፤ በድኅረ ፈተና አንብቦ የመረዳት ችሎታና አንብቦ የመረዳት ንዑስ ክሂሎች፣ በድኅረ የጽሑፍ መጠይቅ ግለመር ማንበብ የሙከራ ቡድኑ ተማሪዎች ከቁጥጥር ቡድኑ ተማሪዎች ጉልህ የሆነ ልዩነት አሳይተዋል (P= <0.05)፡፡ ይህም ውጤት በድጋፍ ብልሀቶች መማር የተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት ችሎታና ግለመር ማንበብን ከማሻሻል አኳያ ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳለው ጠቁሟል፡፡ በተገኙት ውጤቶች በመመስረት የመፍትሄ ሀሳቦችና የጥናት ጥቆማዎች ተሰጥተዋል

Description

Keywords

በአማርኛ ቋንቋ አንብቦ የመረዳት ችሎታ

Citation