በሚቄ እና በአንዘቸ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት የመማር ተነሳሽነት እና የውጤት ተዛምዶ (በአስረኛ ክፍል ጉራጌኛ አፈፈት ተማሪዎች ተተኳሪነት)
No Thumbnail Available
Date
2023-10
Authors
Journal Title
Journal ISSN
Volume Title
Publisher
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ
Abstract
የዚህ ጥናት ዋነኛ ዓላማው የጉራጊኛ ቋንቋ አፈ-ፈት ተማሪዎች አማርኛን በሁለተኛ ቋንቋነት ለመማር ያላቸውን ተነሳሽነትና የትህርት ውጤት ተዛምዶ መፈተሸ ነው፡፡ ጥናቱ የተካሄደው በጉራጌ ዞን በእኖር ኤነር መገር ወረዳ ውስጥ ከሚገኙት ትምህርት ቤቶች በሚቄና በአንዘቸ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በ2015 ዓ.ም በመማር ላይ ያሉት 80 (ሰማኒያ) የአስረኛ ክፍል ተማሪዎች ላይ ነው፡፡ ተጠኚ ተማሪዎችም በእድል ሰጭ የናሙና አመራረጥ ዘዴ ተመርጠዋል፡፡ የፅሁፍ መጠይቅና ፈተና በመረጃ መሰብሰቢያነት የተመረጡ ሲሆን ከተጠኚ ተማሪዎች በፅሁፍ መጠይቅና በፈተና የተሰበሰቡ መረጃዎች በፒርሰን የተዛምዶ መወሰኛ ተተንትኖ ተብራርቷል፡፡ በጥናቱ መረጃ ትንተና መሰረት የተገኘው ውጤት አማርኛን በሁለተኛ ቋንቋነት የሚማሩ ተማሪዎች አማርኛን በሁለተኛ ቋንቋነት የመማር ተነሳሽነት እና በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት መካከሌ ዝምድና የታየው ከውህዳዊ ተነሳሽነት ጋር ብቻ (የፒ ዋጋ 0.000) ነው፡፡ ሌላው አማርኛን የመማር ተነሳሽነት በትምህርት ቤትና በትምህርት ቤት መካከል ልዩነት አልታየም፡፡ የጥናቱ ውጤት መነሻ በማድረግ የተማሪዎችን አማርኛ ቋንቋ የመማር ተነሳሽነት ለማሻሻሌ አማርኛ ቋንቋ የሚያስተምሩ መምህራን ትምህርቱን ሲያቀርቡ የተማሪዎችን ፍላጎት በሚያነሳሳ መልኩ ቢያቀርቡ እና በሁለተኛ ቋንቋ የመማር ተነሳሽነት በፆታ ልዩነት እንዳይፈጠር የወንድና የሴት ተማሪዎች ፍላጎት በመለየት ድጋፍ ቢደረግላቸው የተማሪዎች ሁለተኛ ቋንቋ የመማር ተነሳሽነት ሊሻሻሌ ይችላል የሚሉትን የመፍትሔ ሀሳቦች ተቀምጧል፡፡
Description
Keywords
የጉራጊኛ ቋንቋ አፈ-ፈት