ትብብራዊ መማር የመጻፍ ችሎታን ለማሻሻል ያለው አሰተዋፅኦ (አማርኛን በሁለተኛ ቋንቋነት በሚማሩ በወላይታ ዞን በዳሞትጋሌ ወረዳ በጋቼኖ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በአስረኛ ክፍል (ተተኳሪነት)

No Thumbnail Available

Date

2023-09-02

Journal Title

Journal ISSN

Volume Title

Publisher

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ

Abstract

የጥናቱ ዋና ዓላማ በትብብራዊ መማር የመጻፍ ችሎታ ላይ ያለው ሚና አማርኛን በሁለተኛ ቋንቋነት በሚማሩ በወላይታ ዞን በዳሞትጋሌ ወረዳ በጋቼኖ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በአስረኛ ክፍል ተተኳርነት በመፈተሽ የመጻፍ ችሎታን ለማሻሻል ያለውን አሰተዋፅኦ መፈተሽ ነው፡፡ዓላማውንም ለማሳካት ጥናቱ የተከተለው ሙከራዊ ምርምር ሲሆን ከመተንተኛ ዘዴዎች አንጻር ደግሞ መጠናዊ ምርምርን ተከትሏል፡፡የጥናቱ ተሳታፊዎችም በጋቼኖ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚማሩ የአስረኛ ክፍል ተማሪዎች ብዛት 416 ሲሆኑ ከእነዚህም ለጥናቱ ናሙናነት በYemane(1977) ፎሩሙላ ተጠቅሜ የመረጥኳቸው ተማሪዎች ብዛት 203 ናቸው። ከነኚህም መካከል 156 ተማሪዎች ወላይተኛ አፍ-ፈት ሲሆኑ የቀሩት 47 ተማሪዎች አማርኛ አፍ-ፈት ናቸው፡፡አማርኛ አፍ-ፈት የሆኑት የ47ቱ ተማሪዎች የፈተና ውጤት ከጥናቱ ውጪ ተደርጓል፡፡በዚህ መሰረት 156 ተማሪዎችን በጥናቱ ለማሳተፍ አስቤ ነበር፡፡ሆኖም ከ156 ወላይተኛ አፍ-ፈት ተማሪዎች መካከል 8 ተማሪዎች ቅድመ ትምህርት ፈተናውን ባለመፈተናቸው የድህረ ትምህርት ፈተና ውጤታቸው ከጥናት ውጪ ተደርጓል፡፡የተመረጡ ተማሪዎች በሁለት ቡድን ተመድበው በቁጥጥር ቡድኑ 74 እንደዚሁም በሙከራ ቡድኑ 74 በአጠቃላይ የ148 ተማሪዎች የፈተና ውጤት የጥናቱ ናሙና በመምረጥ ሙከራዊ ጥናቱ ተካሄዷል፡፡ቀጥሎም የሙከራ ቡድን ተማሪዎች በትብብራዊ መማር ዘዴን ለመተግበር የተዘጋጀላቸውን የመለማመጃ ጥያቄዎችን ለተከታታይ አምስት ሳምንታት በሳምንት ሁለት ክፍሌ ጊዜ ከተማሩ በኋላ ድህረ ፈተና ተሰጥቷል፡፡ውጤቱም በድምዳሜያዊ ገላጭ ስታቲስቲክ በቲ-ቴስት(ቲ= -3.78) የp ዋጋ(0.001) ሆኗል፡፡በአጠቃላይ በሁለቱ ፈተናዎች ያለው የውጤት ልዩነት በጉልህነት ደረጃ ሲታይ፣ከፍተኛ የሆነ ልዩነት አሳይቷል፡፡የፈተና ውጤት የሚያሳየው በትብብራዊ መማር የተማሪዎች የመጻፍ ችሎታን ከማሻሻል አንጻር ከፍተኛ ሚና እንዳለው በዚህ ጥናት ተረጋጧል፡፡የትንተናው ውጤት እንዳሚያመለክተውም የሙከራ ቡድን ተማሪዎች ከቁጥጥር ቡድን ተማሪዎች የበለጠ ውጤት አስመዝግበዋል፡፡ገላጭ መረጃው እንደሚያመለክተው የቅድመ ትምህርት ፈተና አማካይ ውጤት 52.81 ሲሆን የድህረ ትምህርት ፈተናው አማካይ ውጤት 59.23 ነው፡፡በቅድመና በድህረ ትምህርት ፈተናዎች መካከል ያለ የአማካይ ውጤት ልዩነት 6.42 ሆኗል፡፡ይህም ውጤት ትብብራዊ መማር የመጻፍ ችሎታን ለማሻሻል ያለው አሰተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑን ያሳያል፡፡በመሆኑም የተማሪዎችን የመጻፍ ችሎታን ለማሻሻል ትብብራዊ የማስተማሪያ ዘዴ የተሻለ እንደሁነ ከጥናቱ መረዳት ተችሏል፡፡

Description

Keywords

Citation