ሂደት ተኮር አቀራረብ የተማሪዎችንት የመጻፍ ችሎታ እና ተነሳሽነት ለማሻሻል ያለው አሰተዋጽኦ (በጉራጌ ዞን በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በጅማ ወለኔ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በ9ኛ ክፍል ተተኳሪነት)
dc.contributor.advisor | ግርማ ገብሬ (ዶ/ር) | |
dc.contributor.author | የሰራሽ አደራው | |
dc.date.accessioned | 2024-09-26T06:09:09Z | |
dc.date.available | 2024-09-26T06:09:09Z | |
dc.date.issued | 2024-07 | |
dc.description.abstract | ይህ ጥናታዊ ጽሁፋ ዋነኛ ዓላማ አድርጎ የተነሳው የሂደት ተኮር የቋንቋ ማስተማር ዘዴ የተማሪዎችየመጻፍ ክሂል ችሎታ እና ተነሳሽነት ከማሻሻል አንጻር ያለውን አስተዋጽኦ ለመፈተሽ ነው፡፡ ጥናቱም ከፊል ሙከራዊ ሲሆን፣ የተካሄደውም በደቡብ ክልል በጉራጌ ዞን በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በሚገኘው በጅማ ወለኔ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነው፡፡ በትምህርት ቤቱ ከሚገኙ ተማሪዎች መካከል የ9ኛክፍል ተማሪዎች በአመቺ የናሙና ስልት ከተመረጡ በኋላ፣ በተራ ዕጣ የናሙና አመራረጥ ስልት በአንድ መምህር የሚማሩ ሁለት ምድብተማሪዎች ተለይተው በቅድመ ፈተናው ሂደት ተሳትፈዋል፡፡ ከሁለቱ ምድቦች መካከል በቅድመ የመጻፍ ክሂል ፈተና ተቀራራቢ አማካይ ውጤቶች ያስመዘገቡ ሁለት ምድቦች ከተለዩ በኋላ በተራ የዕጣ ናሙና ስልት አንዱ የሙከራ ሌላኛው የቁጥጥር ቡድን ሆኖ በጥናቱ ውስጥ እንዲሳተፍ ተደርጓል፡፡ በመረጃ መስብሰቢያ ዘዴነት ፈተና እና የጽሑፍ መጠይቅ ሥራ ላይ ውለዋል፡፡ ፈተናው፣ ቅድመ እና ድኅረ ፈተናን ያካተተ ነው፡፡ ቅድመ ፈተናው የተሰጠበት ዓላማ ተማሪዎች ከሙከራ ጥናቱ በፊት ያላቸውን የመጻፍ ክሂል ውጤት ተቀራራቢ መሆን አለመሆኑን ለመፈተሽ ሲባል ነው፡፡ የድኅረ ፈተናው ዓላማ ደግሞ የሙከራ እና የቁጥጥር ቡድን ሆነው የተመረጡት ተማሪዎች በተለያዩ የማስተማሪያ ዘዴዎች የመጻፍ ክሂልን ከተማሩ በኋላ በመካከላቸው ጉልህ ልዩነት መኖር አለመኖሩን ለመፈተሽ ነው፡፡ በሌላ በኩል የጽሑፍ መጠይቅ የተማሪዎቹን የመጻፍ ተነሳሽነት ለመለካት የቀረበ ነው፡፡ ተተኳሪ የሆኑት ተማሪዎች ከመጻፍ ልምምዱ በፊት (ቅድመ ጽሑፍ መጠይቅ) እና በኋላ (ድኅረ የጽሑፍ መጠይቅ) እንዲሞሉ ተደርጓል፡፡ በቅድመ ፈተና እና በቅድመ የጽሑፍ መጠይቅ የተገኙ ውጤቶች በዳግም ናሙና ቲ-ቴስት ትንተና ዘዴ እንዲሁም በድኅረ ፈተና እና በድኅረ የጽሑፍ መጠይቅ የተገኙ ውጤቶች በባዓድ ናሙና ቲ-ቴስት ትንተና ዘዴ እንዲሰሉ ተደርጓል፡፡ የተገኙት ውጤቶች እንደሚያመለክቱት በቅድመ ፈተና እና በቅድመ የጽሑፍ መጠይቅ ተመጣጣኝ አማካይ ውጤቶች የተመዘገበባቸው ቡድኖች፣ በድኅረ ፈተና ይዘት፣ አደረጃጀት፣ ቃላት፣የቋንቋ አጠቃቀም እና ሥርዓተ አጻጻፍ እና በድኅረ የጽሑፍ መጠይቅ ተነሳሽነት የሙከራ ቡድኑ ተማሪዎች ከቁጥጥር ቡድኑ ተማሪዎች ጉልህ የሆነ ልዩነት አሳይተዋል።ይህም ውጤት የሂደት ተኮር የቋንቋ ማስተማር ዘዴ የተማሪዎችን የመጻፍ ክሂል ችሎታ እና ተነሳሽነት ከማሻሻል አኳያ ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳለው ሊጠቁም ችሏል፡፡ ከመጻፍ ክሂልችሎታ እና ተነሳሽኘት አንጻር የተገኙት ውጤቶች ላይ በመመስረት ማብራሪያ እንዲሰጥባቸው ከተደረገ በኋላ፣ የሂደታዊ ዘዴ የመፃፍ ትምህርት አቀራረብ የተማሪዎችን የመፃፍ ክሂል ለማዳበር ጥሩ አስተዋፅዖ ያለው መሆኑ በጥናቱ ተረጋግጧል፡፡ መምህራን ጥሩ ግንዛቤ ኖሯቸው በክፍል ውስጥ በተገቢው ሁኔታ መተግበር እንዲችሉ የሚያደርጋቸው በቂ ስልጠና ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ የመፍትሄ ሀሳቦች እና የጥናት ጥቆማዎች እንዲቀርቡ ተደርጓል። | |
dc.identifier.uri | https://etd.aau.edu.et/handle/123456789/3477 | |
dc.language.iso | am | |
dc.publisher | አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ | |
dc.title | ሂደት ተኮር አቀራረብ የተማሪዎችንት የመጻፍ ችሎታ እና ተነሳሽነት ለማሻሻል ያለው አሰተዋጽኦ (በጉራጌ ዞን በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በጅማ ወለኔ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በ9ኛ ክፍል ተተኳሪነት) | |
dc.type | Thesis |