በብሪቲ 2ኛ ደረጃ መሰናዶ ትምህርት ቤት አፋቸዉን በኦሮምኛ የፈቱ የ10ኛ ክፍል ተማሪዎችን የሚያስተምሩ መምህራን በአማርኛ ቋንቋ የመናገር ክሂል የክፍል ዉስጥ አተገባበር ፍተሻ

No Thumbnail Available

Date

2023-09

Journal Title

Journal ISSN

Volume Title

Publisher

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ

Abstract

ይህ ጥናት ዋና ትኩረቱ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በኩዩ ወረዳ በብሪቲ ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት በኦሮምኛ ቋንቋ አፋቸውን የፈቱ የ10ኛ ክፍል ተማሪዎችን የሚያስተምሩ መምህራን በአማረኛ ቋንቋ የመናገር ክሂል የክፍል ውስጥ አተገባበርን ማጥናት ነው፡፡ ይህን ጥናት በሚገባ የታቀደለትን ግብ እንዲያስገኝ ለማስቻል መጠናዊና አይነታዊ (ቅይጥ) የምርምር ዘዴን የተጠቀመ ሲሆን የተሰበሰቡትን መረጃዎች በቁጥር ካስቀመጠ በኋላ በሚገባ በገለጻ መልክ አብራርቶዋል፡፡ የትምህርት ቤቱን አመራረጥ በወረዳው የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ስራ ላይ የሚገኘው አንድ ስለሆነ በጠቅላይ ናሙና አመራረጥ ተመርጧል፡፡የጥናቱ ተተኳሪ መምህራንም በጠቅላይ ናሙና አመራረጥ ተመጧል፡፡ ተማሪዎችም በአስረኛ ክፍል ውስጥ ከሚገኙ ሶስት ምድቦች በዕጣ ንሞና ዘዴ ተመርጧል፡፡ በዚህ ሁኔታ የተፈለገውን መረጃ ለማግኘት የተመረጡትን ተተኳሪዎች መሰረት በማድረግ የክፍል ውስጥ ምልከታ፣ የጽሁፍ መጠይቅና የቃል መጠይቆች ተከናውነዋል፡፡ ይህም ማለት የክፍል ምልከታውን በክፍል ውስጥ በመገኘት የመምህርና የተማሪዎች የንግግር ቋንቋ አተገባበር ሂደታቸው የታየ ሲሆን የጽሁፍ መጠይቁን ደግሞ ለተማሪዎች በመስጠት እንዲሞሉ ከተደረገ በኋላ መምህራን ደግሞ የቃል መጠይቁን እንዲ መልሱ ተደርጓል፡፡ በምልከታ፣ በጽሁፍ መጠይቅና በቃል መጠይቅ ከተገኘው መረጃ ትንተና ውጤት ለመረዳት እንደ ተቻለው መምህራን የእለቱን ትምህርት ከማቅረባቸው በፊት አላማን በግልጽ በማናገር ሂደት ብዙ ጊዜ ጥሩ ቢሆኑም ግን የሚቀር ነገር እንዳለ ያሳያል፡፡ በክፍል ውስጥ የመማርማስተማር ሂደት ተማሪዎችን ያሳተፈ አለመሆኑ፤ መምህራን በንግግር ትምህርት ወቅት የተማሪዎች ተሳትፎ እንዲያድግ አለማድረጋቸው፤ ተማሪዎች ክርክር፣ ጭውውትና ውይይት እንዲያደርጉ አለማድረጋቸው፤ መምህራን ሁሉም ተማሪዎች እኩል ተሳትፎ እንዲኖራቸው አለማስቻላቸው፤ ሁሉም ተማሪዎች የንግግር ልምምድ እንዲያደርጉ አለማድረጋቸው፤ ተማሪዎች እርስ በርስ የመወያየት ባህል እንዲኖራቸው አለማድረግ፤ ተማሪዎች ሀሳባቸውን በነጻነት እንዲገለጹ አለማበረታታቸው፤ክፍል ውስጥ ተማሪዎች የግል፣ የቡድንና የጥንድ ስራዎችን እንዲሰሩ አለማስቻላቸው፤ ስዕሎች፣ ፎቶ ግራፎችና ቅርጻ ቅርጾችን በመጠቀም ተማሪዎች ንግግር እንዲያቀርቡ አለማድረጋቸው፤ ለመናገር የሚፈሩ ተማሪዎችን ለማበረታታት አለመሞከራቸው ለማረጋገጥ ተችሎዋል፡፡ በአጠቃላይ ከላይ የቀረቡትን ጉዳዮች መሰረት በማድረግ የመማር ማስተማር ሂደቱ ከመጀመሩ በፊት አላማን ግልጽ ማድረግ፣ ተማሪዎች የንግግር ልምምድ እንዲያደርጉ ማድረግ፣ ሁሉንም ተማሪዎች እኩል ማሳተፍ፣ ተማሪዎች እርስ በርስ የመወያየት ባህሪ እንዲኖራቸው ማድረግ፣ ተማሪዎች ሀሳባቸውን በነጻነት መግለጽ እንዲችሉ ማድረግ፣ ፎቶ ግራፎችና ስዕሎችን በመጠቀም ተማሪዎች ሀሳባቸውን እንዲገልጹ ቢደረግ በማለት የመፍትሄ ሀሳቦች ለማቅረብ ተሞክሯል፡፡

Description

Keywords

አማረኛ ቋንቋ የመናገር ክሂል፡በኦሮምኛ ቋንቋ አፋቸውን የፈቱ

Citation