አፊቸውን በወላይትኛ ቋንቋ የፈቱ የግልና የመንግስት 9ኛ ክፍል ተማሪዎች በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት የጽህፈት ክሂል ችሎታ ንጽጽራዊ ጥናት በወላይታ ዞን በአረካ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ ተተኳሪነት

No Thumbnail Available

Date

2022-06

Journal Title

Journal ISSN

Volume Title

Publisher

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ

Abstract

የዚህ ጥናታዊ ጽሁፍ ዋና አላማ በአረካ ከተማ አስተዳደር አፊቸውን በወላይትኛ ቋንቋ የፈቱ የግልና የመንግስት ትምህርት ቤት የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች የጽሕፈት ክሂል ችሎታቸው ምን ላይ እንደሚገኝ እና የትኞቹ የተሻለደረጃ እንደሚኙ መለየት በንጽጽር መመልከት ነው፡፡ጥናቱንም ከግብ ለማድረስ አጥኝዋ በዋናነት መጠናዊ ምርምር የተጠቀመች ሲሆን በደጋፊነት አይነታዊ ምርምር ተጠቅማለች፡፡ የመረጃ ምንጮች በተጠኝዎች የተፃፈ ድርሰቶችና የተሞላ የጽሐፍ መጠይቆች ናቸው፡፡ መረጃዎቹም በቁጥር የመረጃ ትንተና በገላጭ ንድፍ አቀራረብ በንጽጽር ትንተና ተደርጎባቸዋል፡፡ ጥናቱም ጥቅል ናሙና ዘዴ በመጠቀም 130 ተማሪዎች አፊቸውን በወላይትኛ ቋንቋ የፈቱ የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች መረጃ ተሰብስቧል፡ ከተጠኝዎቹም 65 የግል ትምህርት ቤት ተማሪዎች ሲሆኑ 65 ተማሪዎች የመንግስት ትምህርት ቤት ናቸው፡፡ ከጥናቱ ተሳታፈዎች የተሰበሰበው መረጃ በጥንቃቄ ከተተነተነ በኋላ የተገኘው ውጤት በቃላት አጠቃቀምና ምርጫ፣ በሰዋስው አጠቃቀም፣ በአንቀጽ አደረጃጀት፣ በፊደል ቅርጽ አጣጣልና አጠቃቀም የግል ትምህርት ቤት ተማሪዎች ከመንግስት ትምህርት ቤት ተማሪዎች የተሻለ ሆነው መገኘታቸውን የጥናቱ ውጤት ያሳያል፡፡ በስርዓተ-ነጥብ አጠቃቀምም የግል ትምህርት ቤት ተማሪዎች ከመንግስት ትምህርት ቤት ተማሪዎች የተሻለ መሆናቸው በጥናቱ ተረጋግጧል፡፡በመሆኑም የጥናቱ ግኝትን መሠረት በማድረግ ሁለቱም ትምህርት ቤቶች ያላቸውን የክሂል ክፍተት እንዲያጠቡ የመምህሩ ሚና ከፍተኛ በመሆን ተማሪዎች የግልና የቡድን ስራ እንዲሰሩ በማድረግ አንደ ተማሪ ከሌላው እየተማረ የክሂሌ እውቀት ክፍተታቸውን የሚሞላበትን መንገድ ማመቻቸት ቢቻል የተሻለ ነው፡፡ እንደሁም መምህራን በጽህፈት ትምህርት ጊዜ በተማሪዎች ላይ ጫና ሳይፈጥሩ ተማሪዎቹ በፈለጉት ርዕስ ላይ ድርሰት እንዲጽፉ የሚያደርጉበት መንገድ ቢያመቻቹ፡፡ መምህራን ተማሪዎች የፃፈትን ድርሰቶች አይተው ችግራቸውን እንዲቀርፉ ግብረ-መልስ መስጠቱ ለተማሪዎቹ የጽህፈት ክሂል ማደግ የበኩለን አስተዋጽኦ ያበረክታል በሚል ጥናቱ ተቋጭቷል ፡፡

Description

Keywords

አፊቸውን በወላይትኛ ቋንቋ የፈቱ ተማሪዎች

Citation