አፋቸውን በኦሮምኛ ቋንቋ የፈቱ ተማሪዎች በአማርኛ ቋንቋ፣ ክፍለ ጊዜ ያላቸው የክፍል ውስጥ ተሳትፎ እና የውጤት ተዛምዶ (በጊንጪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት)

No Thumbnail Available

Date

2023-09

Journal Title

Journal ISSN

Volume Title

Publisher

Addis Ababa University

Abstract

የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ በኦሮምኛ ቋንቋ አፋቸውን የፈቱ ተማሪዎች በአማርኛ ቋንቋ ክፍለ ጊዜ በሚያደርጉት የክፍል ውስጥ ተሳትፎና በአማርኛ ቋንቋ ውጤታቸው መካከል ያለውን ተዛምዶ መመርመር ነው፡፡ ይህን ዓላማ ለማሳካት ተዛምዷዊ የጥናት ንድፍን ተግባራዊ ተደርጓል፡፡ የጥናቱ ተሳታፊዎች በጊንጪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተማሩ 48 የዘጠነኛ ከፍል ተማሪዎች ናቸው፡፡ ትምህርት ቤቱ በአመቺ የንሞና ስልት የተመረጠ ሲሆን ተማሪዎች ደግሞ በጠቅላይ የንሞና ስልት በጥናቱ ተካተዋል፡፡ ከ48 ተማሪዎች በአማርኛ ቋንቋ ክፍለ ጊዜ ያላቸውን ተሳትፎ በምልከታና በጽሑፍ መጠይቅ እንዲሁም የአማርኛ ቋንቋ ውጤታቸውን ደግሞ በአማርኛ ቋንቋ ፈተና ተሰብስቧል፡፡ መረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያዎቹ (የጽሑፍ መጠይቁና የአማርኛ ቋንቋ ፈተናው) መረጃ ለመሰብሰቢያነት ከማገልገላቸው በፊት በፍተሻ ጥናት (Pilot Study) መረጃዎች ተሰብስበው፣ መረጃዎች በክሮንባኽ አልፋ ተፈትሸው የተገኘው ውጤት ከ0.7 በላይ በመሆናቸው (አስተማማኝ በመሆናቸው) ለዋናው ጥናት መረጃ መሰብሰቢያነት አገልግለዋል፡፡ ከዚያም ጥናቱ ይዟቸው የተነሳውን መሰረታዊ ጥያቄዎች ለመመለስ ፒርሰን የተዛምዶ መወሰኛ፣ የቀላል ድህረታዊ እና የነጻ ናሙና ቲቴስት ስሌቶች አማካይነት የተሰበሰቡ መረጃዎች ተተንትነዋል፡፡ በትንተናው ውጤትም በአማርኛ ቋንቋ ክፍለጊዜ የክፍል ውስጥ ተሳትፎ እና በአማርኛ ቋንቋ ውጤት መካከል ጉልህ የሆነ አዎንታዊ ተዛምዶ (r=.642፣ P<.01፣ ባለሁለት ጫፍ) እንዳለ እና የተዛምዶ ደረጃውም ከፍተኛ እንደሆነ የፒርሰን የተዛምዶ መወሰኛ ፍተሻው አሳይቷል፡፡ ነጻ ተለዋዋጩ (በአማርኛ ቋንቋ ክፍለጊዜ የክፍል ውስጥ ተሳትፎ) ጥገኛ ተለዋዋጩን (የአማርኛ ቋንቋ ውጤትን) 41.2% እንደሚገልጸው የቀላል ድህረታዊ ትንታኔው ውጤት (R2 = .412፣  = .642፣ F (1፣ 47) = 32.267፣ t = 5.680፣ p = .000) አሳይቷል፡፡ የወንድና የሴት ተማሪዎች የክፍል ውስጥ ተሳትፎ አማካይ ውጤቶች መካከል ልዩነት አለመኖሩን የነጻ ናሙና ቲ-ቴስት ትንታኔው (t (46) = .776, p = 0.442) ያሳዬ ሲሆን የአማርኛ ቋንቋ ውጤታቸው መካከል ያለውን ልዩነት ተፈትሾ የሴትና የወንድ ተማሪዎች በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት አማካይ ውጤቶች መካከል ጉልህ ልዩነት (t (46) = .301, p = .765) አለመኖሩን በጥናቱ ተረጋግጧል፡፡ ከጥናቱ ግኝት በመነሳት መምህራን የተማሪዎችን የክፍል ውስጥ ተሳትፎ እንዲጨምር የበኩላቸውን አስተዋጽዖ ቢያበረክቱ፤ መምህራን የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል ተማሪዎችም እንዲሳተፉ በማነቃቃትና አሳታፊ ማስተማሪያ ዘዴዎችን በመከተል ተሳትፏቸውን እንዲጨምር ቢያደርጉ፤ የክፍል ውስጥ ተሳትፎ እና የትምህርት ውጤት ካላቸው ከፍተኛ ዝምድና አንጻር ተማሪዎች የክፍል ውስጥ ተሳትፏቸውን በማሳደግ ውጤታቸውን ማሳደግ እንዲችሉ የሥርዓተ ትምህርት አዘጋጆች መማሪያ መጻሕፍትንና የመምህር መምሪያዎችን ሲያዘጋጁ ተማሪዎች እንዲሳተፉ ምቹ የሆነና የሚያበረታታ እንዲሆን ትኩረት ቢያደርጉ እና በሁለቱም ጾታዎች ያለው የተሳትፎ ምጥጥን ተጠናክሮ እንዲቀጥል ቢደረግ የሚሉ አስተያየቶች በአጥኚው ቀርበዋል፡፡

Description

Keywords

በኦሮምኛ ቋንቋ አፋቸውን የፈቱ

Citation