በጉራጌ ዞን በጉመር ወረዳ መንግስታዊ በሆኑ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርትቤቶች የሚያስተምሩ የአማርኛ ቋንቋ መምህራን የአንብቦ መረዳት ብልሃቶች የክፍል ውሰጥ አተገባበር (በ9ኛ ክፍል ተተኳሪነት)

No Thumbnail Available

Date

2023-09

Journal Title

Journal ISSN

Volume Title

Publisher

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ

Abstract

የጥናቱ ዋና ዓላማ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርትቤቶች የአማርኛ ቋንቋ መምህራንን የአንብቦ መረዳት ብልሃቶች የክፍል ውስጥ አተገባበር መመልከት ነው፡፡ ለዚህ ጥናት ተሳታፊ እንዲሆኑ የተመረጡት በጉመር ወረዳ በጀንቦሮ እና አረቅጥ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርትቤቶች በ2015ዓ.ም 9ኛ ክፍል አማርኛ ቋንቋ ትምህርት በማስተማር ላይ የሚገኙ መምህራን ሁሉም ናቸው፡፡ ለጥናቱ መረጃ መሰብሰቢያ የሚያገለግሉ መሳሪያዎች የጽሁፍ መጠይቅና ምልከታ ናቸው፡፡ የመምህራኑን የቅድመ ንባብ ፣ንባብ ጊዜና የድህረንባብ ብልሃቶችን የክፍል ውስጥ አተገባበርና ግንዛቤ ለመፈተሸ የሚያስችል ቅጽ ምልከታው ከተከናወነ በኋላ መረጃው ተሰብስቧል፡፡ በምልከታና በጽሁፍ መጠይቅ የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያዎች የተገኙ መረጃዎች በመጠናዊና በአይነታዊ የምርምር ዘዴ ተተንትነዋል፡፡ በጥናቱ የተገኘው ውጤት በሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርትቤቶች የአማርኛ ቋንቋ መምህራን የአንብቦ መረዳት ብልሃቶችን ተግባራዊ ከማድረግ አኳያ በአጠቃላይ የምልከታው ውጤት ምን እንደሆነ አመልክቷል፡፡ በተመሳሳይ መምህራኑ ስለቅድመ ንባብና የንባብ ጊዜ ብልሃቶች የክፍል ውስጥ አተገባበር ምን እንደሆነ አሳይቷል፡፡ በጥናቱ የተገኘው ውጤት ጥናቱ የሚመለከታቸው መምህራን የአንብቦ መረዳት ብልሃቶች የክፍል ውስጥ አተገባበር ዝቅተኛ እንደሆነ ያሳያል፡፡ እንዲሁም በመምህራኑ የአንብቦ መረዳት ብልሃቶች የክፍል ውስጥ ትግበራ ላይ ተግዳሮቶችን ለይቷል፡፡ በመጨረሻም ከጥናቱ ውጤትና ድምዳሜ በመነሳት የመፍትሄ ሃሳቦችና አስተያየቶች ተሰጠተዋል፡፡

Description

Keywords

አንብቦ መረዳት ብልሃቶች፡አማርኛ ቋንቋ

Citation