በስልጥኛ አፋቸውን የፈቱ ተማሪዎች በአማርኛ ድርሰት ሲጽፉ የሚፈጽሟቸው የስህተት ዓይነቶችና የስህተት ምንጮች ትንተና (በዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት)

No Thumbnail Available

Date

2023-09

Journal Title

Journal ISSN

Volume Title

Publisher

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ

Abstract

የጥናቱ ዋና ዓላማ አፋቸውን በስልጥኛ ቋንቋ የፈቱ የዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች በአማርኛ ቋንቋ ድርሰት ሲጽፉ ሚፈጽሙትን የስህተት ዓይነቶችንና የስህተት ምንጮችን መፈተሸ ነው፡፡ በመሆኑም ተማሪዎቹ የሚፈጽሟቸው ዋና ዋና የስህተት ዓይነቶች የትኞቹ ናቸው? ለስህተት የሚዳርጋቸው ዋና ዋና የተጽዕኖ ምንጮችስ ምን ምን ናቸው? ችግሩን ለመቀነስ የሚቻለውስ እንዴት ነው? የሚሉትን የጥናቱን ጥያቄዎች ለመመለስ ነው፡፡ ለዚህም በ2015 ዓ/ም በስልጤ ዞን ሌራ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመማር ላይ ከነበሩ ከሁለት መቶ ስምንት (208) በስልጥኛ ቋንቋ አፈ-ፈት ከሆኑ ተማሪዎች ውስጥ በአንድ መቶ አራት (104) ተማሪዎች ላይ ትኩረት በማድረግ ጥናቱ ተካሄዷል፡፡ እነዚህም ተማሪዎች እኩል እድል ሰጪ ንሞና የሆንውን የእጣ ንሞናን ዘዴ በመጠቀም የተመረጡ ናቸው፡፡ ለጥናቱ መረጃዎችን ለመሰብሰብ በዋናነት አገልግሎት ላይ የዋለው የተማሪዎች የድርሰት ፈተና ነው፡፡ በተለያዩ መንገዶች የተገኙትን መረጃዎች ዓይነታዊ የመረጃ መተንተኛ ዘዴ በመጠቀም ገለፃዊ በሆነ መልኩና የስህተቶች መጠን፤ በጽህፍ መጠይቅ፣ በቃለ-መጠይቅና በድርሰት ጽህፍ ፈተና የተሰበሰቡትን ውጤቶች አሀዛዊ በሆነ መልኩ መጠናዊ የምርምር ዘዴ አተናተን በመጠቀም የተተነተነ ነው፡፡ በዚህ አተናተን ዘዴም ለጥናቱ መሰረታዊ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ተሞክሯል፡፡ ከድርሰት ትንተናው በተገኘው መረጃ መሰረት አራት አብይ የስህተት አይነቶች ተለይተዋል፡፡ በነዚህም ውስጥ ከተቆጠሩት ከአጠቃላይ አራት ሽህ አምስት መቶ ሃምሳ ስምንት (4558) ስህተቶች መካከል ሶስት ሽህ ስድስት መቶ ስልሳ (3660) ወይም (80.3%) በቋንቋ አጠቃቀም ስህተቶች ምድብ፣ ስድስት መቶ ስልሳ ሁለት (662) ወይም (14.5%) በቋንቋ አወቃቀር ስህተቶች ምድብ፣ ሁለት መቶ አስራ ሶስት (213) ወይም (4.67%) በስርዓተ-ነጥቦች ስህተቶች ምድብ እና ሀያ ሶስት (23) ወይም (0.5%) መለየት ባልተቻሉ ስህተቶች ምድብ እንደተፈጸሙ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በተጨማሪም ለተማሪዎች በቀረበው ጽሁፍ መጠየቅና ለመምህራን በቀረበው ቃለ-መጠየቅ ጭምር በተሰበሰበው መረጃ መሰረት የተለያዩውጤቶች ተገኝተዋል፡፡ ከድርሰት ጽሁፍ በተሰበሰበው መረጃ የተገኙ አብይ ውጤቶች፤ በቋንቋ አጠቃቀም ሂደት የተመዘገቡ ስህተት ስርጭቶች ናቸው፡፡

Description

Keywords

አፋቸውን በስልጥኛ ቋንቋ የፈቱ

Citation