የ9ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ የመናገር ክሂል የክፍል ውስጥ አተገባበር ግምገማ (በከምባታ ጠምባሮ ዞን ሀደሮ ጡንጦ ወረዳ የመንግሥት ትምህርት ቤቶች ተተኳሪነት)

No Thumbnail Available

Date

2022-06

Journal Title

Journal ISSN

Volume Title

Publisher

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ

Abstract

የዚህ ጥናት ዋና አላማ አራት የመንግሥት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የዘጠነኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ የመናገር ክሂል አተገባበር ግምገማ መፈተሽ ነው፡፡ በዚህ መሠረት በዋናነት በመምህራን ላይ ትኩረት ያደረገ የክፍል ውስጥ የመማር ማስተማር ምልከታ ተከናውኗል፡፡ በተጨማሪም መምህራንና ተማሪዎች የጽሑፍ መጠይቅ እንዲሞሉ ተደርጓል፡፡ በሀደሮ ጡንጦ ወረዳ የሚገኙ 4 የመንግሥት 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በአመቺ ናሙና ተመርጠዋል፡፡ የመማሪያ ክፍሎቹም በዕጣ ናሙና ስልት እንዲመረጡ ተደርጓል፡፡ አራት የአማርኛ ቋንቋ መምህራን በኢላማዊ ናሙና ተመርጠው በጥናቱ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ አንድ መቶ አስራ ሁለት ተማሪዎች በመረጃ ሰጪነት የተሳተፉት እኩል ዕድል በሚሰጠው በቀላል የዕጣ ናሙና ስልት ነው፡፡ የክፍል ምልከታና የዕሁፍ መጠይቅ ለጥናቱ ተግባራዊ የተደረጉ የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴዎች ናቸው። የክፍል ውስጥ የንግግር ክሂል አተገባበር ተፈትሾ ደካማና ጠንካራ ጐኖቹን በመለየት ጠንካራውን ይበልጥ የሚጐለብቱበትን፣ ደካማው የሚሻሻልበት የመፍትሄ ሀሳብ ተጠቁሟል፡፡ መምህራን የንግግር ክሂል ትግበራውን አሰባስበውና ጊዜ ውስደው የተማሪዎችን በራስ የመተማመን መናገር ፍላጐትን የማይቀሳቅስ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ተማሪዎችን የንግግር ችሎታ ለማዳበር ጊዜ ውስደው ሲሰሩ አልታዩም፡፡ ስለዚህ ተማሪዎች ግድየለሽነት ሲታይባቸው ተስተውሏል፡፡ ለመናገር የሚፈሩና አይናፋር ተማሪዎችን ጊዜ ወስደው እንዲዘጋጁ የሚያደርግ ተግባር ያልተፈጸመ መሆኑን ጥናቱ ያሳያል፡፡ በመጨረሻም በጥናቱ ከላይ ለተጠቀሱት ችግሮች የሚመለከታቸው የትምህርት ባለድርሻ አካላት መምህራንና ተማሪዎች ምን ምን ማድረግ እንዳለባቸው የመፍትሄ ሃሳቦችን ጠቁሟል፡፡

Description

Keywords

Citation