በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ ሴቶች ብቻቸዉን እና ወንዶችና ሴቶች አንድ ላይ በሚማሩባቸዉ የግል ትምህርት ቤቶች የዘጠነኛ ክፍል የሴት ተማሪዎች የክፈል ዉስጥ ተሳትፎ ንጽጽራዊ ጥናት

No Thumbnail Available

Date

2004-06

Journal Title

Journal ISSN

Volume Title

Publisher

አዲስ አበባ ዮኒቨርሲቲ

Abstract

የዚህ ጥናት ዋና አላማ ሴት ተማሪዎች ብቻቸዉን ሲማሩና ሴት ተማሪዎች ከወንድ ተማሪዎች ጋር ሲማሩ ያተሳትፎ ሁኔታ በማነጻጸር መመርመር ነዉ፡፡ ጥናቱን ለማካሄድ የአዲስ አበባ ከተማ በአላማ ተኮር የናሙና አመራረጥ ስልት ሲመረጥ የልደታ ማርያም የልጃረዶች ትምህርት ቤትና የልደታ ማርያም የወንዶች ትምህርት ቤት በአመቺ የናሙና አመራረጥ ስልት ተመርጠዋል፡፡ ትምህርት ቤቶቹ ከተመረጡ በኋላ የዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች በአላማ ተኮር የናሙና አመራረጥ ስልት የተመረጡ ሲሆን የዘጠነኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መምህራንም ጠቅላይ የናሙና አመራርጥ ስልትን በመጠቀም ተመርጠዋል፡፡ ለጥናቱ መረጃ መሰብሰቢያነት ምልከታ (በምስል ቀረጻ የታገዘ) በዋና መረጃ መሰብሰቢያነት፤ የፀሁፍ መጠይቅና ቃለ መጠየቅ በአጋዥ የመረጃ መሰብሰቢያነት ተመርጠዉ መረጃዉ ተሰብበዋል፡፡የተሰበሰቡት መረጃዎች በአይነታዊና በገላጭ የመረጃ አተናተን ዘዴ ተተነረትነዋል፡፡ የጥናቱ ዉጤት እንደሚያመለክተዉም ብቻቸዉን የሚማሩ ሴት ተማሪዎች ከወንዶች ጋር ከሚማሩት ሴት ተማሪዎች የተሻለ ተሳታፈ ሆነዉ ተገኝተዋል፡፡ ይህንንም ለማረጋገጥ በምልከታ ፤ በፅሑፍ መጠይቅ እና በቃለ መጠይቅ የተገኙትን መረጃዎች በይዘት በመከፋፈል ያላቸዉን ልዩነት በማነጻጸር የመረጃዉን ዉጤት ለመገንዘብ ተችሏል፡፡በመጨረሻም ሴት ተማሪዎች ብቻቸዉንም ሆነ ከወንድ ተማሪዎች ጋር ሆነዉ በሚማሩበት ጊዜ እጃቸዉን በማዉጣት እንዲሳተፋ ለማድረግ መምህራኑ ቢያበረታቷቸዉ ፤ ሴት ተማሪዎች የተሳሳተ መልስ ሲመልሱ ተማሪዎቹ እንዳይደናገጡ በማድረግ ድጋሚ እንዲሞክሩት ወይም የተሳሳቱትን ጥያቄ እንዲያስተካከሉት እድል ቢሰጣቸዉ ፤በቋንቋ መማሪያ መጻህፍት ላይ ሴት ተማሪዎች መልስ በሚመልሱበት ጊዜም ሆነ በሚሳተፋበት ጊዜ ወንድ ተማሪዎች እንዳይስቁባቸዉ የሚያደርጉ ምክር አዘል የሆኑ ምንባቦች እንዲካተቱ ቢደረግ የሚሉ የሴት ተማሪዎች የክፍል ዉስጥ ተሳትፎ እዲጨምር ለማድረግ ያግዛሉ የተባሉ አስተያየቶች በአጥኚዋል ተሰንዝረዋል፡፡

Description

Keywords

Citation