ትብብራዊ መማር የተማሪዎችን የመፃፍ ክሂል፣ ማህበራዊ ክሂልና የመፃፍ ተነሳሽነት ለማሳደግ ያለው ሚና (አማርኛን በሁለተኛ ቋንቋነት በሚማሩ በባሌ ዞን በዘይበላ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ7ኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት)

No Thumbnail Available

Date

2009

Journal Title

Journal ISSN

Volume Title

Publisher

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

Abstract

የጥናቱ ዓላማ ትብብራዊ መማር የተማሪዎችን የመፃፍ ክሂል፣ ማህበራዊ ክሂልና የመፃፍ ተነሳሽነት ለማሳደግ ያለውን ሚና መፈተሽ ነው፡፡ ጥናቱም የተከናወነው አማርኛን በሁለተኛ ቋንቋነት በሚማሩ በባሌ ዞን በዘይበላ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ7ኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት ነው፡፡ ጥናቱ ከፊል ፍትነታዊነት መሰል የምርምር (Quasi Experimental Research) ስልትን ተከትሏል፡፡ የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያዎቹም ፈተና፣ የጽሑፍ መጠይቅና ቃለመጠይቅ ናቸው፡፡ የፈተናዎቹ ውጤት በt- ቴስት አማካይነት ተነጻጽሯል፡፡ ውጤቱንም ለማነጻጸር የስህተት ይሁንታ መጠኑ በ0.05 (5%) ባለሁለት ጫፍ ነው፡፡ ከዋናው ጥናት በፊት የቁጥጥር ቡድኑና የሙከራ ቡድኑ የነበራቸውን የቅድመሙከራ የመጻፍ ክሂል ችሎታ ከወዲሁ ለማወቅ የቅድመትምህርት ፈተና ተፈትነዋል፡፡ በቅድመትምህርት የፈተና ውጤታቸውም በአማካይ የቁጥጥር ቡድኑ 52.67 እንደዚሁም የሙከራ ቡድኑ 52.42 ሆኗል፡፡ ይህ ውጤት ሁለቱም ቡድኖች በድህረትምህርት ፈተና የመጻፍ ችሎታቸው ተቀራራቢ መሆኑን ጠቁሟል፡፡ በቀጣይ የቁጥጥር ቡድኑ በተለመደው መንገድ፣ የሙከራ ቡድኑ በትብብራዊ መማር ለአንድ ሴሚስተር ያህል ከተማሩ በኋላ ሁለቱም ቡድኖች የድህረትምህርት ፈተና ተፈተኑ፡፡ የተሳታፊዎቹ የድህረትምህርት ፈተና ውጤት በአማካይ የቁጥጥር ቡድኑ 53.13፣ እንደዚሁም የሙከራ ቡድኑ 59.38 ነው፡፡ ይህ የውጤት ልዩነት በt-ቴስት ስታትስቲክስ (p= 0.046) ጉልህ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ እንደዚሁም ትኩረት በተደረገባቸው ንዑሳን የመጻፍ ክሂሎች ላይ የሙከራ ቡድኑ የቅድመና የድህረትምህርት አማካይ የፈተና ውጤቶች ልዩነት በt-ቴስት ስታትስቲክስ ተሰልቶ ውጤቱም በተሰጡ ቃላትና ሀረጋት ዐረፍተነገር በማዋቀር ንዑስ ክሂል (p= 0.001)፣ የዐረፍተነገር ክፍሎችን ቅደም ተከተል በማስተካከል ንዑስ ክሂል (p= 0.00)፣ ጅምር ዐረፍተነገሮችን በማጠናቀቅ ንዑስ ክሂል (p= 0.000)፣ አያያዥ ቃላትን ተጠቅሞ ዐረፍተነገርን በማደራጀት ንዑስ ክሂል (p= 0.000)፣ ጅምር አንቀጽን በማጠናቀቅ ንዑስ ክሂል (p= 0.00) ጉልህ ሆኗል፡፡ በሌላ በኩል ትብብራዊ መማር የተማሪዎችን ማህበራዊ ክሂልና የመጻፍ ተነሳሽነትን ለማሳደግ ያለው ተፅዕኖ ምን እንደሚመስል በጽሑፍ መጠይቅና በቃለመጠይቅ አማካይነት መረጃ ተሰብስቧል፡፡ ማህበራዊ ክሂልን በተመለከተ የጽሑፍ መጠይቁን ከሞሉ መላሾች መካከል 81.18% የሚሆኑት ማህበራዊ ክሂላቸው እንዳደገ በምላሻቸው ጠቁመዋል፡፡ ይህም ውጤት በt- ቴስት ተሰልቶ 4.31 አማካይ ውጤት አሳይቷል፡፡ ይህ ውጤት ደግሞ Peta (2001) ባስቀመጠው ቀመር መሰረት ከፍተኛ ነው፡፡ ከቃለመጠይቁም የተገኘው ምላሽ የጽሑፍ መጠይቁን ውጤት የሚያጠናክር ሆኗል፡፡ እንደዚሁም የመጻፍ ተነሳሽነትን በተመለከተ የጽሑፍ መጠይቁን ከሞሉ መላሾች መካከል 83.83% የሚሆኑት የመጻፍ ተነሳሽነታቸው እንዳደገ በምላሻቸው ጠቁመዋል፡፡ ይህም ውጤት በt- ቴስት ተሰልቶ 4.4 አማካይ ውጤት አሳይቷል፡፡ አሁንም ይህ ውጤት Peta (2001) ባስቀመጠው ቀመር መሰረት ከፍተኛ ነው፡፡ ከቃለመጠይቁም የተገኘው ምላሽ የጽሑፍ መጠይቁን ውጤት የሚያጠናክር ሆኗል፡፡ በአጠቃላይ ከጽሑፍ መጠይቁና ከቃለመጠይቁ ከተገኘው መረጃ መገንዘብ የተቻለው ትብብራዊ መማር የተማሪዎችን ማህበራዊ ክሂልንና የመጻፍ ተነሳሽነትን ለማሳደግ ያለው ተፅዕኖ ጉልህ መሆኑን ነው፡፡ በመሆኑም ትብብራዊ መማር የተማሪዎችን የመፃፍ ክሂልን፣ ማህበራዊ ክሂልንና የመፃፍ ተነሳሽነትን ለማሳደግ ያለው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ፣ የሚመለከታቸው አካላት ለማስተማሪያ ዘዴው ትኩረት ሊሰጡት እንደሚገባ አጥኚው ይጠቁማል፡፡

Description

Keywords

Citation