የአማርኛ አፍ-ፈት ተማሪዎች በአማርኛ ጽሑፍ ላይ የሚፈፅሟቸው ስህተቶች እና የስህተት ምንጭ ትንተና፤ በአዲስ አበባ ከተማ በተመረጡ ሁለት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት በ የአምላክሥራ ሕይወት

dc.contributor.advisorአስራቴን, ሙሉሰው (ዶ/ር)
dc.contributor.authorሕይወት, የአምላክሥራ
dc.date.accessioned2018-06-14T07:54:42Z
dc.date.accessioned2023-11-09T04:06:39Z
dc.date.available2018-06-14T07:54:42Z
dc.date.available2023-11-09T04:06:39Z
dc.date.issued2008-09
dc.description.abstractየዚህ ጥናት ዋና ዓላማ የአማርኛ አፍ-ፈት ተማሪዎች በአማርኛ ጽሑፍ ላይ የሚፈጽሟቸውን ስህተቶችና የስህተት ምንጮች መመርመር ነው፡፡ ተጠኚ ተማሪዎቹ በአዲስ አበባ ከተማ በሁለት የተመረጡ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ የዘጠነኛ ክፍል አማርኛ አፍ-ፈት ተማሪዎች ናቸው፡፡ በጥናቱ የተካተቱት 100 ተማሪዎች ሲሆኑ የተመረጡትም በቀላል የእጣ ንሞና ዘዴ ነው፡፡ ለጥናቱ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን ለማግኘት በተጠኚ ተማሪዎቹ በሁለት ዙር 157 ድርሰቶች እንዲጽፉ ተደርጓል፡፡ በነዚህ ድርሰቶች መሰረት ተማሪዎቹ በጽሑፋቸው ለይ የሚፈጽሟቸውን ስህተቶች ለመለየት ተችሏል፡፡ በተጨማሪም በተጠኚ ተማሪዎቹ ከተሞሉ የጽሑፍ መጠይቆች እና ከአማርኛ ቋንቋ መምህራን ቃለ መጠይቆች መረጃ ተሰብስቧል፡፡ በነዚህ መረጃዎች ለተማሪዎች ስህተት መፈጸም ምክንያት ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮችን ለመለየት ተችሏል፡፡ከድርሰት እርማት በተገኘው መረጃ መሰረት ጠቅላላ የስህተቶች ብዛት 1066 ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 478 (44.84) የቋንቋ አጠቃቀም፣ 466 (43.73%) የቋንቋ አወቃቀር እንዲሁም 122 (11.44%) የሥርዓተነጥብ አጠቃቀም ስህተቶች ሆነው ተገኝተዋል፡፡ ተማሪዎች ከጻፏቸው ድርሰቶች እንዲሁም በተማሪዎች እና በመምህራን ከተሞሉ መጠይቆች በተገኙ መረጃዎች መሰረት የስህተቶቹ ምንጮች የማስተማሪያ መሳሪያዎች ዝግጅትና የማስተማሪያ ዘዴ ድክመት እና የስነልቦናዊ ሁኔታዎች ተጽእኖ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡እነዚህን ችገሮች ለማቃለል የማስተማሪያ መሳሪየዎችን አዘገጃጀት እና የማስተማሪያ ዘዴወችን ማሻሻል፤ እንዲሁም ተማሪዎች ትምህርቱን በፍላጎት እንዲማሩ የሚያስችሉ ሁኔታዎችን ማመቻቸት የሚሉ መፍትሄ ሀሳቦች ተጠቁመዋል፡፡en_US
dc.identifier.urihttp://etd.aau.edu.et/handle/123456789/870
dc.language.isoamen_US
dc.publisherአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲen_US
dc.subjectበአማርኛ ጽሑፍ ላይ የሚፈፅሟቸው ስህተቶችen_US
dc.titleየአማርኛ አፍ-ፈት ተማሪዎች በአማርኛ ጽሑፍ ላይ የሚፈፅሟቸው ስህተቶች እና የስህተት ምንጭ ትንተና፤ በአዲስ አበባ ከተማ በተመረጡ ሁለት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት በ የአምላክሥራ ሕይወትen_US
dc.typeThesisen_US

Files

Original bundle
Now showing 1 - 1 of 1
No Thumbnail Available
Name:
የአምላክሥራ ሕይወት.pdf
Size:
667.81 KB
Format:
Adobe Portable Document Format
License bundle
Now showing 1 - 1 of 1
No Thumbnail Available
Name:
license.txt
Size:
1.71 KB
Format:
Plain Text
Description: