መሠረት, ዘላለም ዶ/ርአማረ, አያሌው2019-08-292023-11-092019-08-292023-11-092019-02http://etd.aau.edu.et/handle/123456789/18913ይህ ጥናት በኢትዮጵያ ኦርቶድክስ ተዋሔድ ቤተ ክርስቲያን፣ የጥምቀተ ክርስትና፣ የተክሉሌና የሜሮን ሥርዒተ ክዋኔ ፍክልራዊ ዔይታ በሚሌ የተጠና ነው፡፡ የጥናቱ መረጃዎች የተሰበሰቡት በዋናነት በሰነድች ምርመራ፣ በምሌከታ፣ በቃሇ መጠይቅና በቡዴን ውይይት ከአምስት የተመረጡ አብያተ ክርስቲያናት ሲሆን፤ በመረጃ አቀባይነት የተመረጡትም ሉቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ የሰንበት ተማሪዎች፣ ካህናት፣ የእምነቱ ተከታይ ወጣቶች፣ አረጋውያንና እናቶች ናቸው፡፡ በነዘህ ዖዳዎች የተሰበሰቡት መረጃዎች ጥናቱ በኢኦተቤ የጥምቀተ ክርስትና፣ የተክሉሌና የሜሮን ሥርዒተ ክዋኔ ፍክልራዊ ገጽታን ማሳየት ዒሊማ አዴርጎ በመነሣቱ የሥርዒተ ክዋኔዎቹን ፍክልራዊ ጉዲዮች ሇማሳየት የክዋኔ /performance/ ቲዎሪ ዖዳን ተጠቅሟሌ፡፡ በክዋኔ ንዴፇ ሀሳብ አቅጣጫ መሠረትም በገሊጭ የምርምር ስሌት መረጃዎች ተተንትነው ቀርበዋሌ፡፡ የጥምቀተ ክርስትና፣ የተክሉሌና የሜሮን ሥርዒት ክዋኔ ወቅት የሚታዩ ሃይማኖታዊና ባህሊዊ ተግባራት ተምሳላታቸው ተተንትኗሌ፡፡ የክርስቲያን ሌጆች ሔፃናት ወንድች በተወሇደ በ40ኛው ቀናቸው፤ ሴቶች ዯግሞ በ80 ቀናቸው ክርስትና ይነሣለ፡፡ በተጨማሪም ማንኛውም ሰው በየትኛውም ዔዴሜ ክሌሌ ሊይ ከተማረና ካመነ መጠመቅ እንዯሚችሌ በጥናቱ ተረጋግጧሌ፡፡ በዘህ ዔሇት ተጠማቂዎች በጥምቀት ከመንፇስ ቅደስ ዲግመኛ ተወሌዯው ጸጋቸውን የሚቀበለበት ቀን ነው፡፡ ወዱያውም የተሇያዩ የአካሌ ክፌልቻቸው ሜሮን ይቀባለ፡፡ ሃይማኖታዊ ሥርዒቱ እንዲሇሆኖ፣ ማኅበረሰቡም ከሃይማኖታዊው ሥርዒት ውጪ በሌማዴ ዖወትር ከሚመገበው እንጀራ ሊይ ተጠማቂዎችን ያንከባሌሎቸዋሌ፣ ይህም ወዯፉት እንጀራ ይስጥህ፣ሀብም ሁን፣ የተሰጠህን ጸጋ በተግባር የምታውሌ ፣ ያዴርግህ ማሇታቸው እንዯሆነ ጥናቱ አመሊክቷሌ፡፡ የክርስቲያን ሌጆች በሃይማኖት ውስጥ ኖረው፣ በዴንግሌና ቆይተው፣ ሇጋብቻ ሲዯርሱ ተክሉሌ ይፇጽማለ፡፡ በተክሉሊቸውም ወቅት ሜሮን ይቀባለ፤ ይህም ጋብቻቸው በመንፇስ ቅደስ የተባረከ የተቀዯሰ ጋብቻ እንዯኾነ የሚረጋገጥበት ነው፡፡ የክርስትና እናትና አባት ተግባር ዒሊማው ሃይማኖትን ማስተማር ቢሆንም በማኅበረሰቡ ባህሊዊ ዛምዴና የመፌጠሪያ ትስስሩ በሌጦ መታየቱን በጥናቱ ግኝት ተረጋግጧሌ፡፡ ይህም ጥምቀተ ክርስትና ሃይማኖታዊና ፍክልራዊ ተግባራትን የሚያሳይ መሆኑን ሇመረዲት ተችሎሌ፡፡ የጥምቀተ ክርስትናና የሜሮን ሥርዒተ ክዋኔ ፊይዲው ተጠማቂዎች ዲግመኛ ከውኃና ከመንፇሥ ቅደስ ተወሌዯው፣ የእግዘኣብሓር የጸጋ ሌጅነታቸው እንዱረጋገጥ መዴረግ እንዯኾነ ጥናቱ አሳይቷሌ፡፡ በተጨማሪም የተክሉሌ ጋብቻ የቤተሰብ አንዴነት፣ የጋብቻ ዖሊቂነት፣ የትውሌዴ ቀጣይነት እንዱኖር ፊይዲ ያሇው መኾኑን ሇማወቅ ተችሎሌ፡፡ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሥርዒተ ክዋኔ ወጥ ሆኖ ሳሇ በክርስትና ምክንያት ምዔመናኑ ከአኗኗራቸው የራሳቸውን ሌማድች ሲከውኑ ይስተዋሊሌ፤ እነዘህም ተጠማቂ ሔፃናትን እንጀራ ሊይ ማንከባሇሌ፣ እንጀራውን ቆራርሶ ሇታዲሚዎች መብሊት፣ የክርስትና ዴግስና አበሌጆች ሲያገቡ የሚሰጡ ስጦታዎች በሌማዴ የሚከወኑ ናቸው፡፡ እነዘህና በየጊዚው የሚታዩትን ጨምሮ በፍክልራዊ ገጽታቸው የሚታዩ ሆነዋሌ፡፡am“የጥምቀተ ክርስትና፣ የተክሉሌና የሜሮን ሥርዒተ ክዋኔ ፍክልራዊ ዔይታ በኢትዮጵያ ኦርቶድክስ ተዋሔድ ቤተክርሰቲያን”Thesis