ገብሬ, ቴዎድሮስ (ረ/ፕ)አለበል, ቴዎድሮስ2018-06-132023-11-092018-06-132023-11-092006-06http://etd.aau.edu.et/handle/123456789/673ይህ ጥናት ልጅነት በማሕሌት እና አለንጋና ምስር፤ ሥነ ልቡናዊ ንባብ በሚል የተደረገ ነው፡፡ የጥናቱ ዘዴ በይነ-ቴክስታዊ ሲሆን ስልቱ ደግሞ ፍካሬ ነው፡፡ ጥናቱ በተመረጡት ቴክስቶች ውስጥ ልጅነት ከሥነ ልቡና ንድፈ ሃሳቦች አንጻር ቢፈተሽ መልካም ነው በሚል ዕምነት የተደረገ ነው፡፡ በቴክስቶቹ የተቀረጹ ልጆች ማኅበረ-ልቡናዊና ሳይኮሴክሿል ማንነት፣ Oedipus complex እና የልቡና ፍርቅነት፣ የጨቅላነት ግንትሮሽ እና የሁለት ሰብዕናዎች መቃየጥ እንዲሁም ከልዩ ልዩ ሚቶሎጂዎች የተቀዱ መባያዎች ሰብዕናን መርምሮ ለማሳየት ትኩረት የተደረገባቸው ነጥቦች ናቸው፡፡ ጥናቱ ወዲህ በቴክስቶቹ ውስጥ የተቀረጹ ገጸ-ልጆች የብቸኝነት፣ የመከዳትና የመጣል ስሜት የሚስተዋልባቸው እንደሆኑ፣ ወዲህ ደግሞ የአሳዳጊዎቻቸው ሚና አፍራሽ መሆኑ፣ የጨቅላነት ሳይኮሴክሿል ዕድገት ፊክሴሽንና sadistic displacement ማደሪያዎች እንደሆኑ ተብራርቷል፡፡ ስለሆነም፣ በእነዚህና በትንተናው ውስጥ በ“ተዘነቁ” ሃሳቦች ልጆቹ ማኅበረ-ባህላዊ ኃላፊነትን መሸከም የማይችሉ እንደሆኑ ለማጠቃለል ተሞክሯል፡፡ በመጨረሻም በቴክስቶቹ ውስጥ ልጆቹ የተቀረጹት፣ ማኅበረ-ባህላዊ ሥርዓቶችና ተፈጥሯዊ ማንነቶች በመጎራበት ነው ብሎ ማጠቃለል ይቻላል፡፡ IVamሥነ ልቡናዊ ንባብ“ልጅነት” በማሕሌትና አለንጋና ምስር፤ ሥነ ልቡናዊ ንባብThesis