ግርማ ገብሬ (ዶ/ር)አካል ግርማ2023-12-212023-12-212023-09http://etd.aau.edu.et/handle/123456789/1137የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ የዘጠነኛ ክፍል በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሂደት ወዘውግ ተኮር የማስተማር ዘዴ በተማሪዎች ድርሰት የመፃፍ ችሎታ ላይ ያለው ሚና ፈትሿል፡፡ ይህን አላማ ከግብ ለማድረስ ሙከራ ቢጤ የጥናት ንዴፍ (Quasi experimental research design) በመጠቀም ለምፈተሸ ይቻል ዘንድ ተማሪዎችን በቁጥጥር እና በሙከራ ቡድን በሁለት በመክፈል ጥናቱ ተካሂዷል፤ በመሆኑም ምሁራን ባነሷቸው ሀሳቦች በማጎልበት በዋነኝነት ፈተና በደጋፊነት ደግሞ የፅሁፍ መጠይቅና ምልከታ በመጠቀም መረጃ በመሰብሰብና መረጃውን የቲ-ቴስት የመተንተኛ ዘዴ በመጠቀም በአግባቡ ተደራጅተው ትንተና የተደረገባቸው ናቸው፡፡ የተገኘውም ውጤት እንዳመለከተው በሂደታዊ ዘውግ የተማሩት የሙከራ ቡድኑ ተማሪዎች በልማዳዊው (በመርሃ ትምህርቱ) ከተማሩት የቁጥጥር ቡድን ተማሪዎች በተሻለ የመጻፍ ክሂላቸው እንዳሻሻሉ ፣ በቂ ደረጃ ላይ እንደደረሰ ፣ የመጻፍ ተሳትፏቸው የተሻሻለ መሆኑን አመልክቷሌ ፡፡ በመሆኑም ሂደታዊ ዘውግ የመፃፍ ማስተማሪያ ዘዴን በመጠቀም የተማሪዎችን የመጻፍ ክሂልን ማሻሻል፣ በቂ ደረጃ ላይ ማዴረስና ተሳትፎቸውን መጨመር ተማሪዎችን ለደረጃቸው የሚመጥን የመጻፍ ክሂል ችሎታ ላይ ማዴረስ ይቻላል የሚል አስተያየት ላይ ተደርሷሌ ፡፡ በዚህም በወጉ ያረሰ እንደልቡ ጎረሰ እንደሚባለው መምህራን ጊዜያቸውን ፣ ጉልበታቸውንና እውቀታቸውን በተገቢ ሁኔታ አዲዱስ አሰራሮችን በመጠቀም በተማሪዎች የመፃፍ ክሂል ላይ መጠቀም ከቻሉ የሚጠበቀውን ውጤት ማምጣት እንደሚቻል በጥናቱ ማረጋገጥ ተችሏል፡፡amድርሰት የመፃፍ ችሎታሂደት ወዘውግ ተኮር የማስተማር ዘዴ በተማሪዎች ድርሰት የመፃፍ ችሎታ ላይ ያለው ሚና (በአጋሮ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ9ኛ ክፍል ተተኳሪነት)Thesis