ዳዊት ፍሬሕይወት (ዶ/ር)በደገሉ ሮቢ2023-12-072023-12-072023-09-11http://etd.aau.edu.et/handle/123456789/347የዚህ ጥናት ዋና አላማ ማህበረ-ስሜታዊ ብልሃት ከተማሪዎች አንብቦ የመረዲት ችሎታ ጋር ያለውን ተዛምዶ መፈተሽ ነው፡፡ አላማውን ከግብ ለማድረስም ተዛምዶዊ የጥናት ስሌት ተግባራዊ ሆኗል፡፡ የጥናቱ ተሳታፉዎች በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን በእሉ ገላን ወረዲ ከሚገኙ ሶስት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል የኦዲ ብሲል ትምህርት ቤት ነው፡፡ ይህ ትምህርት ቤት አመቺ የንሞና ዘዳ በመጠቀም ተመርጧሌ፡፡ በዚህ ትምህርት ቤት ውስጥ በ2015 ዓ.ም በአምስት የመማሪያ ክፍልች ውስጥ ተማሪዎች ተመድበው ትምህርታቸውን የሚከታተሉ ሲሆን ከአምስቱ ምዴብ (ክፍል) ውስጥ 10ኛ “D” የመማሪያ ክፍል ተማሪዎችን በቀላል የዕጣ ንሞና ዘዴ ተወስደው በአጠቃላይ 80 ተማሪዎች የጥናቱ ተሳታፉዎች እንዱሆኑ ተዯርጓል፡፡ ከጥናቱ ተሳታፉዎችም ማህበረ-ስሜታዊ ብልሃት ከተማሪዎች አንብቦ የመረዳት ችሎታ ጋር ያለውን ተዛምዶ በተመለከተ በአንብቦ መረዳት ችሎታ ፈተናና በፅሁፍ መጠይቅ አማካይነት መረጃው ተሰብስቧሌ፡፡ የተሰበሰበው መረጃም በአማካይ ውጤት፣ በመደበኛ ልይይትና በፒርሰን የተዛምዶ ስሌት ተሰልቶ ተተንትኗል፡፡ የጥናቱ ውጤት እንዳመለከተውም ማህበረ-ስሜታዊ ብልሃት ከተማሪዎች አንብቦ በመረዳት ችሎታ ጋር ያለው ተዛምዶ አዎንታዊ እንደሆነ አመላክቷል፡፡ የተዛምዶው መጠንም ጭንቀትን መቀነስ (r = 0.846, p= .001) ሲሆን ጥያቄ መጠየቅ(r = 0.642, p= .001) ሆኖ ተገኝቷል፤ በትብብር መስራት (r = 0.701, p= .001) መሆኑን አሳይቷል፡፡ ጭንቀትን መቀነስ፣ ጥያቄ መጠየቅና በትብብር መስራት ከአንብቦ የመረዳት ችሎታ ጋር ያላቸው የተጋርቶ መጠንም R2= 0.521 ወይም 52.1% ነው፡፡ ይህም የሚያመሊክተው የተማሪዎች ማህበረ-ስሜታዊ ብልሃት ከአንብቦ የመረዳት ችሎታቸው ጋር ያለው ተዛምዶ R2= 0.521 በመሆን ከፍተኛ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ስለዚህ ከጥናቱ ውጤት በመነሳት ማህበረ-ስሜታዊ ብልሃት ከአንብቦ መረዳት ችሎታ ጋር አዎንታዊ የሆነ ተዛምድ አለ ከሚለው ድምዳሜ ላይ ተደርሷል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ መምህራን ማንበብን በሚያስተምሩበት ወቅት ማህበረ-ስሜታዊ ብልሃትን ከግምት ውስጥ በማስገባት ቢያስተምሩ ተመራጭ ነው፡፡ ከዚህም ባሻገር ይህ ርዕሰ ጉዲይ አዎንታዊ እንዲሆን የሚያደርጉ ስራዎች በለሎች ተለውጦዎች፤በተለያዩ ትምህርት ቤቶች ላይ በርከት ባሉ ናሙናዎች ወደፊት ቢፈተሹ ከዚህ የተሸለ ውጤት ሊገኝ ይችላል የሚል ሃሳብ ተመልክቷል፡፡amማህበረ-ስሜታዊ ብልሃት እና የአንብቦ መረዳት ችሎታ ተዛምድ፤ በአስረኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነትThesis