ጌታቸው እንዳላማው (ዶ/ር)ቀለሟ ታደሰ2023-12-222023-12-222023-09http://etd.aau.edu.et/handle/123456789/1147የጥናቱ ዋና አላማ ቡድናዊ መማር የኢ-አፍፈት ተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት ችሎታና የማንበብ ተነሳሽነት ለማጎልበት ያለውን ጠቀሜታ በከፊል ፍትነታዊና አይነታዊ ንድፈመመርመር ነው፡፡ ጥናቱ በዴራ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ9ኛ ክፍል ደረጃ ተካሂዷል፡፡ ትምህርት ቤቱ በአመቺ ናሙና ዘዴ የተመረጠ ሲሆን የጥናቱ ተተኳሪዎች እንደየ ቋንቋቸው ተመድበው ከሚማሩ16 ምድብ አፍ መፍቻ ቋንቋቸው ኦሮምኛ ቋንቋ የሆነ በመጀመሪያው ፈረቃ የሚማሩ ተማሪዎች መካከል 9ኛሀናለ ምድብ ናቸው፡፡ ጥናቱ ከፊል ሙከራዊ ጥናት እንደመሆኑ በቀላል የእጣ ናሙና አመራረጥ 9ኛሀ የሙከራና ለየቁጥጥር ቡድን ሆነው በጥናቱ ተካተዋል፡፡ የሁለቱም ምድብ ቁጥር እኩል ሲሆን በ9ኛ ሀናለ 42 በድምሩ 84 ተማሪዎች በጥናቱ ተካተዋል፡፡ ጥናቱ የተካሄደው ለ12 ክፍለ ጊዜያት ሲሆን የክፍል ውስጥ ልምምድ የተከናወነው የሙከራ ቡድኑ በቡድናዊ መማር ስልት፣የቁጥጥር ቡድኑ በተለምዶዊው ተምረዋል፡፡ የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያዎች ፈተና የጽሁፍ መጠይቅ፣ቡድን ተኮርና ምልከታ ናቸው፡፡ የመረጃዎቹ አስተማማኝነት በእኩል ክፍይ ዘዴና በክሮንባኧ አልፋ ተሰልቷል፡፡ መረጃዎች ከተጣሩ በኋሊ SPSS.V20 በመጠቀም በስታስቲክስና በአይነታዊ መተንተኛ መንገድ ተተንትነዋል፡፡ ቁጥጥርና ሙከራ ቡድኖቹ በቅድመ አንብቦ የመረዳት ፈተና በገላጭ ስሌትና በቲ ቴስት ተፈትሾ(ፒ>0.05) በሁለቱ ቡድኖች መካከልጉልህ የአማካይ ውጤት ሌዩነት አለመኖሩ ተረጋግጧል፡፡ ነገር ግን በቅድመና ድህረ ፈተና አማካይ ውጤት ጉልህ (ፒ<0.05) ብልጫ ማሳየቱን ማወቅ ተችሏል፡፡ ሙከራ ቡድኑበቅድመ የማንበብ ተነሳሽነት መጠይቅ የሰጡትን ምላሾች አማካዩ ተወስዶ ሲታይ በድምሩ (66.8%)ቱ አለመስማማትን ሲገልጹ በአንጻሩ (33.2%) መስማማትን ገልጸዋል:: በድህረ የማንበብ ተነሳሽነት መጠይቅ ምላሽ ግን በድምሩ (73.9%)ቱ በጣም መስማማትን በአንጻሩ (39.3%) አለመስማማትን ገልጸዋል፡፡ በቡድን ተኮር ውይይቱ ከተማሪዎች የተገኘው ምላሽ የሚያሳየው ቡድናዊ መማር አንብቦ የመረዳትና የማንበብ ችሎታቸውን ለማጎልበት ጠቃሚ መሆኑንና በምልከታ የተገኘው መረጃም የሚያሳየው ቡድናዊ መማር ውጤታማ መሆኑን ነው፡፡ በመረጃው ውጤት ማረጋገጥ የተቻለው ቡድናዊ መማር ስልት ለኢ-አፍ ፈት ተማሪዎች አንብቦ የመረዳት ችሎታና የማንበብ ተነሳሶትን ለማጎልበት ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው እንድሆነ ነው፡፡ በጥናቱ ግኝት መነሻነትም አስተያየት ተሰቷል፡amአንብቦ የመረዳት ችሎታ፡የማንበብ ተነሳሽነት ለማጎልበትበቡድን መማር ስልት የኢ-አፍፈት ተማሪዎችን አንብቦ መረዳትና የማንበብ ተነሳሽነት ለማጎልበት ያለውን ጠቀሜታ፤በዴራ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ9ኛ ክፍል ተተኳሪነትThesis