አስፋው, ዘሪሁንቦጋለ, ብርሃኑ2020-11-022023-11-092020-11-022023-11-092003-06http://etd.aau.edu.et/handle/123456789/22985ይህ ጥናት መሣል- ባህላዊ የግጭት አፈታት ሥርዓት በአንፆኪያ ገምዛ ወረዳ በሚል ርዕስ የቀረበ ነው፡፡ የግጭት አፈታቱን አጠቃላይ ገ ታ እና ባላጋራዎች ሲዳኙ የቻሉበትን ምክንያት ለማወቅ መረጃዎችን በወረዳው ውስጥ ከሚገኙ ሽሆች፤ ካዳምች፤ሽማግሌዎች፤ በተቋሙ ከተዳኙ ግለሰቦች፤ ወንጀል መርማሪ ፓሊሶች እና ከፍርድ ቤት ዳኞች ተሰብስቧል፡፡ የመረጃ ሰብሰባዉም ተፈጥሮአዊ እና ቅንብር ተፈጥሮአዊ መቼቶችን በመጠቀም በቃለ መጠይቅ እና በምልከታ የተከናወነ ሲሆን፤ መረጃዎችም በቪዲዮ፤ በፎቶ፤ በጽሁፍ እና እና በመቅረጸ ድምጽ ተይዘዋል፡፡ የተገኙ መረጃዎች በገላጭ እና በይዘት ትንተና ስልት ተተንትነዎል፡፡ በዚህ መሰረት ከተራ ጠብ እሰከ ግድያ ያሉ የግጭት አይነቶች እንደሚፈቱ የጥናቱ ግኝት ያመለከታል፡፡ በተጠናው አካባቢ የሚከሰቱትም የግጭት አይነቶች ከንብረት ጋር የተያያዙ (መሬት፤ ድንበር፤ የግጦሸ ቦታ፤ የመስኖ ውኃ፤ ከብት ዝርፈያ፤ ቤትና ሰብል ቃጠሎ፤ አትክልት እና ሰብል መቂረጥ ) ፤ የቤተሰብ ጠብ (ከጋብቻ፤ከልጆች እና ከዉርስ) ወንጀል (ግድያ፤ድብደባና ስድብ)፤ተራ ወንጀሎእ (ሰርቆትና ማታለል ፤ ቤት ድብደባና ክህደት) ችና የቡድን ጠብ (የብሔረሰብ) መሆናቸውን ጥናቱ አሳይቷል፡፡ ለግጭቶቹ መፈጠር ምክንያት የሚሆኑት ማኅበራ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች፤ እለታዊ ጠብ እና ቂም በቀል እንደሆኑም ጥናቱ አመልክቷል፡፡amመሣል- ባህላዊ የግጭት አፈታት ሥርዓት በአንፆኪያ ገምዛ ወረዳThesis