ሰላማዊት መካ (ረ/ፕሮፌሰር)አንለይ ጥላሁን2025-02-122025-02-122017-10https://etd.aau.edu.et/handle/123456789/4149ነገረ-ህላዌ በተመረጡ የአማርኛ ግጥሞች ውስጥ የሚል ርዕስ የተሰጠው ይህ ጥናት፣ የነገረ-ህላዌ ንድፈ ሃሳብን መሰረት አድርጎ ነፃነት፣ ኃላፊነት፣ ውሳኔ፣ ምርጫ እና ተግባርን በመለየት እነዚህ ጉዳዮች በአማርኛ የግጥም መድበሎች ውስጥ በተካተቱ የተመረጡ ግጥሞች ውስጥ በምን መልኩ እንደተገለጹ ተንትኗል፡፡ ይህን ጥናት ለማከናወን በዓበይትነት የተመረጠው የነገረ-ህልውና ንድፈ-ሃሳብ በመሆኑ በትንተና ዘዴ መረጃዎቹ ተተንትነዋል፡፡ እነዚህ ግጥሞች ከ1980 እስከ 2012 ዓ.ም ከታተሙ አስራ አምስት መድበሎች ውስጥ የተመረጡ ሲሆን ግጥሞቹ በጭብጥ ደረጃ ከላይ የተዘረዘሩትን የሚያሳዩ ናቸው። ጥናቱ፣ የተመረጡት ግጥሞች ‹‹ማደሪያውን ጠርቶ መኖሪያውን›› ወይም በተገላቢጦሽ የሆነ የአንድምታ ትርጉም የያዙ ናቸው፡፡ በአጠቃላይ የጥናቱ ውጤት እንደሚያሳየው፣ ለጥናቱ የተመረጡት የአማርኛ ግጥሞች ውስጥ ጎልተው የታዩት የህልውና ጉዳዮች ነፃነት፣ ኃላፊነት፣ ምርጫ፣ ውሳኔ እና ተግባር ናቸው። በእነዚህ ጉዳዮች ውስጥ የፈጣሪ ህልውና እንዲሁም ዋና ዋና የሕብረተሰብ እሴቶች በመተቸታቸው እንግዳ የሆኑ አዳዲስ እይታዎች ተስተውለዋል፡፡ በአዳዲስ እይታዎቹ አማካኝነትም ግጥሞቹ የነገረ-ህላዌ ጉዳዮችን ያዘሉ ሆነው ተገኝቷል። በመጨረሻም የግጥሞቹ ዋና ማሰሪያ ነፃነት ሆኖ ፖለቲካን፣ እምነትንና ባህልን ሳይጮሁ የሚንዱ፣ እንዲሁም የግለሰብን ነፃነት የሚያፀድቁ መሳሪያዎች መሆናቸው በጥናቱ ታይቷል፡፡amነገረ-ህላዌ በተመረጡ የአማርኛ ግጥሞች ውስጥThesis