ሀሰን, አህመድታደሰ, ፀዳለ2018-06-142023-11-092018-06-142023-11-092007-01http://etd.aau.edu.et/handle/123456789/889ይህ ጥናት ዋነኛ ትኩረቱን ያደረገው በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን በባሶና ወራና ወረዳ ስር በሚገኘው የቀይት ንዑስ ወረዳ ውስጥ በሚከወኑ ሀገረሰባዊ ዕምነቶች ላይ ነው፡፡ የጥናት ወረቀቱ ርዕስ ‘በቀይት ንዕስ ወረዳ የሚከወኑ ሀገረሰባዊ ዕምነቶች’ የሚል ሲሆን በስሩ አምስት ሀገረሰባዊ ዕምነቶች ተዳሰዋል፡፡ እነዚህም ዕምነቶች ጫት መቀቀል፣ ጭዳ፣ አድባር፣ ቦረንትቻ እና አቴቴ/ፈጫሳ ሲሰኙ መነሻቸው፣ ፋይዳቸው፣ ሀይማኖታዊ ትስስራቸው፣ ከበራቸው እንዲሁም በአካባቢው ማህበረሰብ ለዕምነቶቹ ያለው አመለካከት በዚህ የጥናት ወረቀት ውስጥ ተዳሷል፡፡ ዋና አላማውም የእነዚህን ዕምነቶች መነሻ፣ ይዘትና አከባበር ማሳየት ነው፡፡ ለጥናቱ በግብዐትነት ያገለገሉት ከቀዳማይና ካልኣይ ምንጮች የተገኙ መረጃዎች ሲሆኑ በመረጃ መሰብሰቢያነት ደግሞ በዋናነት አገልግሎት ላይ የዋሉት ምልከታና ቃለምልልስ እንዲሁም የቡድን ውይይት ናቸው፡፡ በእነዚህ ሶስት ዘዴዎች ከ23 የመረጃ ሰጪዎች መረጃ የተሰበሰበ ሲሆን መረጃ ሰጪዎቹ የተመረጡት ባሳዩት ፈቃደኝነት ነው፡፡ ከመስክ የተሰበሰቡት መረጃዎች ደግሞ ገላጭ በሆነ የትንተና ዘዴ ተተንትነው እና በአምስት ዋና ዋና ክፍሎች ተከፍለው ቀርበዋል፡፡ መረጃዎቹ የተተነተኑት በCathrine Bell የከበራ አይነቶችን እና በPascal Boyer & Pierre Liénard የከበራ መገለጫዎች ፅንሰ ሀሳቦች ተቃኝተው ነው፡፡ በተገኘው መረጃ መሰረት በተጠኚው አካባቢ የተጠቀሱት አምስት ሀገረሰባዊ ዕምነቶችamየሚከወኑ ሀገረሰባዊ እምነቶችበቀይት ንዑስ ወረዳ የሚከወኑ ሀገረሰባዊ እምነቶችThesis