አየለ ፍቅሬ(ዶ/ር)መስከረም ኪዳነማሪያም2024-06-272024-06-272024-01https://etd.aau.edu.et/handle/123456789/3265ይህ ጥናት በ2008 ዓ.ም ለህትመት በበቃው የአዳም ረታ “የስንብት ቀለማት” ረጅም ልብወለድ የጭብጥ አቀራረብን ፈትሿል። ልብወለድ ያነሳቸው ርዕሰ ጉዳዮች መሠረታዊነት እንደ ጥናታዊ አነሳሽ ምክንያቶች ተወስዷል። ጥናቱ አይነታዊ ዘዴን ተጠቅሟል። ነገረህላዌን ለመተንተኛነትሲጠቀም፣ መዛግብት ወይም ሠነድ ፍተሻና ጥልቅ ንባብ ደግሞ በመረጃ መሠብሰቢያ ዘዴነት ተጠቅሟል።ሁለት የመረጃ ምንጮችንም ተጠቅሟል።እነሱም ቀዳማይና ካልዓይ ናቸው።ቀዳማይ የመረጃ ምንጩ ትንተና የሚካሄድበት የስንብት ቀለማትረጅም ልብወለድ ሲሆን ካልዓይ የመረጃ ምንጮች የምርምር ዘዴ መፃህፍት ፣የንድፈሀሳብና ተዛማጅ ፅሁፎች ናቸው። የልብወለድን ርዕስ ማጤን፣ የገፀባህርያትን ምልልስ/ የእርስበርስ ግንኙነት መመርመር፣ የመቼት ገለጻና የሀሳብ ድግግሞሽ በመረጃ ትንተናው ወቅት ለጭብጥ ትንተናው አገልግሎት ላይ የዋለ የጭብጥ መፈለጊያ ዘዴዎች ናቸው። የስንብት ቀለማት የጊዜ መቼት ከ1960ዎቹ መጀመሪያ እስከ 1980ዎቹ መጨረሻ ባሉት የጊዜ ሀዲድ ላይ የተዘረጋ ሲሆን በእነዚህ ሁለት አስርት ዓመታት ውስጥ የተከሰቱት አበይት ሀገራዊ ክስተቶች የ1966ቱ አብዮት፣ የወያኔና የሻዕቢያ ትግል እንዲሁም የሌሎች ተቀናቃኝ ፓርቲዎች የስልጣን ሽሚያ እንደ ልብወለድ የታሪክ ማስታወሻ ሆነው ቀርበዋል። የመረጃ ትንተናው ሁለት አበይት ክፍሎች ያሉት ሲሆን የመጀመሪያው ክፍል የልብወለድን አብይ ጭብጥ ሁለተኛው ክፍል ደግሞ ንዑሳን ጭብጦችን ይዞል። ሞት ወይም ስንብት የተፈጥሮ ጠባይና አካል መሆኑን ማርዳት የልብወለድ አብይ ጭብጥ ሲሆን “የ ያ ትውልድ ስህተቶች”፣ የመበዳደል አዘሪትና ጭላንጭል ተስፋዎች ደግሞ እንደ ልብወለድ ንዐሳን ጭብጦች ተዳሰዋል። የ ያ ትውልድ ስህተቶች በ1960ዎቹና 1970ዎቹ የኖሩ ወጣቶች የፈጸሟቸውን ፖለቲካዊ ስህተቶች ተመልክቷል። የመበዳደል አዙሪት ደግሞ በገፀባህርያት መካከል የነበሩ ቁርሾዎችና ጥሎች የተዳሰሰበት ክፍል ነው። ጭላንጭል ተስፋዎች ደግሞ1960ዎች እና1970ዎቹ ውስጥ የኖሩ ወጣቶች ከፈጸሟቸው ስህተቶች እንዲሁም በዘመኑ ከነበረው ሀገራዊ ቀውስ በኋላ የታየውን አንጻራዊ ሠላምና መረጋጋት እንዲሁም አዳዲስ የለውጥ ጅማሮዎች የተበሰሩበት ክፍል ነው።የጭብጥ ትንተና በየስንብት ቀለማትThesis