ነጋሣ, ሙሉጌታዋቀዮ, ሐሰን2018-06-112023-11-092018-06-112023-11-092001-06http://etd.aau.edu.et/handle/123456789/361ይህ ጥናታዊ ጽሑፍ ዘጠና በሚሆኑ የአርሲ ኦሮሞ «ዋሰዲ´ አባባሎች ላይ በማተኮር የተሠራ ነዉ፡፡ አባባሎቹ ከምዕራብ አርሲ ዞን ኮፈሌ ወረዳ የተሰበሰቡ ናቸው፡፡ አባባሎቹ በትምህርት ½ በተፈጥሮ ½ በንጽጽር½ በአለመጣጣምና በተለያዩ ጉዳዮች ተከፋፍለው ቀርበዋል፡፡ “ዋሰዲ”ዎቹ (ሶስት ነገሮች) የህብረተሰቡን እውነተኛ ማንነት ½ ፍልስፍና ½ አተያይ ½ የህይወት ጎዳና ½ ስነምግባራዊ እሴቶች ወዘተ አንፃባርቀው ህዝቡ የመተራረም½ የመማማር½የመተሳሰብ½ የመፈቃቀር ወዘተ ባህል እንዳለው የሚያሳዩ ናቸው፡፡ ስለሆነም ይህ ጥበባዊ የሕዝብ ቅርስ ትኩረት አግኝቶ ለምልሞ፤ አብቦና ፍሬ በማፍራት ከትውልድ ወደ ትውልድ በመተላለፍ ፈንታ በተወሰኑ የእድሜ ባለፀጎች አእምሮ ውስጥ እየጠወለገ½ እየቀጨጨ½ እየተረሳ½ እየደበዘዘ ወዘተ ከእነሱ ጋር ወደ መቃብር በመጓዝ ላይ ነው፡፡ ስለዚህ እነዚህን አባባሎች ከመጥፋት ለመታደግ ተጠንተው በተለያዩ ዘዴዎች በማስቀመጥ እስከነ ሙሉ ለዛቸው ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፉበትን ዘዴ መሻት ወቅቱ የሚጠይቀው ታሪካዊ ሥራ መሆኑ የዚህ ጥናት የትኩረት አቅጣጫ ሆኖ ተገኝቷል፡፡enዋሰዲ´ አባባሎች ትንተናየአርሲ ኦሮሞ «ዋሰዲ´ አባባሎች ትንተናThesis