ደረጀ ገብሬጳውሎስ ጋምቡራ2023-12-252023-12-252022-08http://etd.aau.edu.et/handle/123456789/1158የዚህ ጥናት ዋና አላማ አድርጎ የተነሳው በወላይተኛ ቋንቋ በወላይተኛ ቋንቋ አፋቸዉን የፈቱ የሆኑ የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት የአንብቦ መረዲትና የንባብ ልምዴ ችሎታ ላይ ያለውን ሚና መፈተሸ የሚል ነው፡፡ ተሳታፉዎች በደቡብ ክልል በወላይታ ዞን በአረካ ከተማ አስተዲደር አረካ ሙሉ አንደኛ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2015 ዓ.ም ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙ በአጠቃላይ ከእያንዳንዱ ሰክሽን 0.5% በመውሰድ ከ264 ተማሪዎች መካከል በቀላል ወይም በተራ ንሞና አመራረጥ ስልት አማካይነት 132 ተማሪዎችን በተጠኝነት ተመርጠዋል፡፡ ከተሳታፉፊዎች መረጃ የተሰበሰበው በሁለት የተለያዩ የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴዎች ነው፡፡ እነሱም የጽሁፍ ፈተናና የጽሁፍ መጠይቅ ናቸው፡፡ ፈተናዎቹ የአንብቦ መረዳት እና የማንበብ ልምድ ችሎታን ለመለካት ሲያገለግል የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴ በመሆን አገልግሎል፡፡የተሰበሰቡት መረጃዎች አስተማማኝነት ተገቢነትና የውጤት ስርጭት ወጥነት ተሰልቶ ከተረጋገጠ በኋላ ሁሉም መረጃዎች በመጠናዊ ወይም ገላጭ እና ዓይነታዊ ምርምር ዘዴ አማካኝነት ስታትስቲክሶች ተተንትነው ተብራርተዋል፡፡ በመሆኑም የተገኘው መረጃ በስታስቲካሌ ዘዴና በመቶኛ ፐርሰንት በመቀመር መለኪያ /አማራጮች / Likert scale የ“SPSS” ሶፍትዌር መለኪያዎችን በቅንነት የባለሙያ ድጋፍ አማካይነት እንድወጣ ተደርግዋል፡፡ መለኪያዎች /አማራጮች/ Likert scale የመፈተሻ ዘዴዎችን ለመጠቀም የሚያስችል በመሆኑ ተግባራዊ የተደረጉት በመተንተኛ ዘዴዎች ላይ Gray (2004) እና Karl pearson, (1888) ናቸው፡፡ በትንተናው መሰረት በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት የአንብቦ መረዲትና የንባብ ልምዴ ችሎታን በመጠኑ መካከለኛ ሆኖ ተገኝቷል፡፡የአማርኛ ትምህርት የአንብቦ መረዳት ችሎታ ፈተና ዉጤት አማካይ 62.18 ሲሆን የተማሪዎች የንባብ ልምድ አማካይ ዉጤት ዳግሞ 65.73 ነዉ፡፡ እንዴሁም የአንብቦ መረዳት ችሎታ ፈተና ዉጤት የተገኘዉ መደበኛ ልይይት/sd/ 0.247487 ስሆን የተማሪዎች የማንበብ ልምዴ ፈተና ዉጤት የተገኘዉ መደበኛ ልይይት/sd/ ዳግሞ 0.908818 ነዉ፡፡ በትንተናው መሰረት የተገኘ ውጤት የበርካታ ተማሪዎች በማኔስ ላይ ሲሆን ዳግሞ ጥቂቶቹ በማደግ ላይ መሆኑን አስቀምጧል፡፡amበወላይተኛ ቋንቋ አፋቸዉን የፈቱበወላይታ ዞን በአረካ ከተማ ሙሉ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት በወላይተኛ ቋንቋ አፋቸዉን የፈቱ የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት የአንብቦ መረዳትና የንባብ ልምድ ችሎታ ፍተሻThesis