መካ, ሰላማዊትተስፋዬ, ምሕረት2022-02-032023-11-092022-02-032023-11-092003-06http://etd.aau.edu.et/handle/123456789/29873ይህ ጥናት ከጣና ቂርቆስ የአባቶች እና የእናች የአንድነት ገዳም አመሰራረት ጋር ተያያዥነት ያላቸው ተረኮች በመተንተን እና ቁሳዊ ባህሎቹ የሚኖራቸውን ተምሳሌት በመመርመር ላይ የተካሄደው ነው፡፡ በጥናቱ ከቤተ መጻሕፍት መረጃዎች በተጨማሪ ጥናቱ ስለሚካሄድበት አካባቢ፣ ከገዳሙ ጋር ተያያዥነት ስላላቸው ተረኮች፣ በገዳሙ ውስጥ ተምሳሌትነት ስላላቸው ቁሳዊ ባህሎች በቃለ መጠይቅ እና በምልከታ መረጃዎች ተሰብስበዋል፡፡ ለጥናቱ አስራ ሁለት መረጃ አቀባዮች የተሳተፉ ሲሆን ከእነዚህ መካከል አራቱ ቁልፍ አቀባዮች ናቸው፡፡ መረጃዎቹም በማስታወሻ፣ በፎቶ ካራ፣ በመቅረፀ ድምፅ ተይዘዋል፡፡ እነዚህን መረጃዎችም በገላጭ የምርምር ዘዴ፣ በተምሳሌታዊ መስተጋብራዊነት ቲዎሪ (Symbolic interactionism theory) ና በተግባራዊ ንድፈ ሀሳብ (Functionalism Approaches) ለመመርመር ተሞክሯል፡፡ ከጥናቱ ጋር ተዛምዶ ያላቸው አስራ አምስት የመጀመሪ ዲግሪ እና አራት የሁለተኛ ዲግሪ ማሟያ ጽሑፎችና የጥናቱ አካባቢም ተቃኝተዋል፡፡amከጣና ቂርቆስየአንድነት ገዳም አመሰራረት ጋር ተያያዥነት ያላቸው ተረኮች እና ቁሳዊ ባህሎች ጥናትThesis