ኃይለሚካኤል, አረጋ (ዶክተር)ደሳለኝ, አሰፉ2018-06-132023-11-092018-06-132023-11-092001-06http://etd.aau.edu.et/handle/123456789/684በቋንቋ መማር-ማስተማር ሂደት የትምህርት መርጃ መሣርያዎች አጠቃቀም ዓቢይ ትኩረት የሚሻ ጉዳይ ነው፡፡ የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ ዓይነታዊ የምርምር ዘዴን ተጠቅሞ በገላጭ ሥልት በአንደኛ ደረጃ ሁለተኛ ዕርከን ትምህርት ቤቶች የአማርኛ ቋንቋ መምህራን የትምህርት መርጃ መሣርያዎች አጠቀቀም ምን እንደሚመስል መፈተሽ ነው፡፡ ይህንን ፍተሻ ለማካሄድ አጥኚዋ በጎንደር ከተማ አስተዳደር ሥር ከሚገኙ የአንደኛ ደረጃ ሁለተኛ ዕርከን ትምህርት ቤቶች መካከል አራቱን በናሙናነት መርጣለች፡፡ የተተኳሪዎች አመራረጥም የምርምር ስልትን በተከተለ መልኩ በአመች፣ በነሲብ እና በግኝት ናሙና አመራረጥ ዘዴዎች ነው፡፡ አጥኚዋ ዋና ዓላማዋን ለመፈተሽ የሚያስችሉ የክፍል ውስጥ የምልከታ ቅፅ፣ የጽሑፍና የቃል መጠይቆችንም ተጠቅማለች፡፡ በስምንት ተተኳሪ የሰባተኛ እና የስምንተኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መምህራን ክፍል ውስጥ በመገኘት ለእያንዳንዱ መምህር የሦስት ሦስት ክፍለ ጊዜያት ምልከታ በማካሄድ፣ ለስምንቱም መምህራን የጽሑፍ መጠይቅ በማስሞላት እና የቃል መጠይቅ በማድረግ መረጃዎች ተሰብስበዋል፡፡ በተጠቀሱት የመረጃ መሰብሰቢያ መሣሪያዎች አማካኝነት መረጃዎቹ ተሰብስበው ከተተነተኑ በኋላ ውጤቶቹ በአብዛኛዎቹ ክፍለ ጊዜያት የመምህራን የትምህርት መርጃ መሣሪያዎች አጠቃቀም (58% እስከ 67%)፣ መምህራን ያለትምህርት መርጃ መሣሪያ በቃል ብቻ ትምህርቱን እንደሚያስተምሩ በተወሰኑት ክፍለ ጊዜያት (33% እስከ 42%) መምህራን በትምህርት መርጃ መሣሪያዎች እንደሚጠቀሙ መረዳት ተችሏል፡፡ የትምህርት መርጃ መሣሪያዎቹ ጥራትና መጠንም በዝቅተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ጥናቱ አሳይቷል፡፡ የተማሪዎች የክፍል ውስጥ ተሳትፎና መስተጋብር ግን በትምህርት መርጃ መሣሪያዎች በተጠቀሙባቸው ክፍለ ጊዜያት በጥሩ ደረጃ እንደሚገኝ በጥናቱ ተረጋግጧል፡፡ ለሚደመጡ፣ ለሚደመጡና ለሚታዩ የትምህርት መርጃ መሣሪያነት የሚያገለግሉ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን በእርዳታ በበቂ ሁኔታ አግኝተዋል፤ ግን በክፍል ውስጥ ለሚካሄደው የቋንቋ መማር-ማስተማር ሂደት አላዋሉትም፡፡ በመማሪያ ክፍሎች ውስጥ ለትምህርት መርጃ መሣሪያነት የሚያገለግሉ የተለያዩ ሰሌዳዎች፣ እንዲሁም ለትምህርት መርጃ መሣሪያ ፍንጭ ሰጪ የሚሆኑ መርሃ ትምህርት እና የመምህሩ መምሪያ የሉም፡፡ መምህራን የሚጠቀሙባቸው መርጃ መሣሪያዎች አንዴ ተጠቅማችሁ ወዲያውኑ ጣሉ የሚል የትምህርት ባለሙያዎች ጣልቃ ገብ አመራር እንዲሁም መምህራኑ በግል ጥረታቸው ለትምህርት መርጃ መሣሪያ መጠቀሚያ በእርዳታ የሚያገኙትን ባጀት የትምህርት ቤቱ አስተዳደር ለሌላ አስተዳደራዊ አገልግሎት ማዋል በዋነኛነት የቀረቡ ድክመቶች ናቸው፡፡ በመጨረሻም በዚህ ጥናት ውስጥ የቀረቡትን ድክመቶች ለማቃለል የሚረዱ የመፍትሄamአንደኛ ደረጃ ሁለተኛ እርከን ትምህርት ቤቶች አማርኛ ቋንቋበጎንደር ከተማ አራት አንደኛ ደረጃ ሁለተኛ እርከን ትምህርት ቤቶች አማርኛ ቋንቋ መምህራን የትምህርት መርጃ መሣሪያዎች አጠቃቀምThesis