አማረ, ጌታሁን ( ዶ/ር)ቴሌ, ሲሳይ2018-06-122023-11-092018-06-122023-11-092007-03http://etd.aau.edu.et/handle/123456789/476የዚህ ጥናት ዋነኛ ዓላማ ከ2001 ዓ.ም. እስከ 2006 ዓ.ም. በሀገር አቀፍ የፈተናዎች ድርጅት ለአጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ በተሰጡት ፈተናዎች ውስጥ ተካተው የሚገኙትን የሰዋስው ጥያቄዎች ይዘትና አቀራረብ መተንተን ነው፡፡ በጥናቱም ዓይነታዊ እና መጠናዊ የምርምር ስልትን በመጠቀም ለጥናቱ ዋና ዋና ጥያቄዎች ምላሽ ተሰጥቷቸዋል፡፡ በሰነድ ፍተሻ የተገኙት መረጃዎች በተዛማጅ ጽሑፍ ክፍል ውስጥ ከተነሱት ንድፈ-ሀሳባዊ ጉዳዮች አኳያ ተተንትነዋል፡፡ በዚህም መሰረት ከ2001 ዓ.ም. እስከ 2006 ዓ.ም. በተሰጡት የአጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ የአማርኛ ቋንቋ ፈተናዎች ውስጥ የቋንቋን አጀማመርና ባህርያት፣ ስነ-ድምጽን፣ ስነ-ምዕላድን፣ ስነ-አገባብን እና ስነ-ፍችን የሚመለከቱ ዋና ዋና ይዘቶች ተካተው እንደሚገኙ ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ በተተኳሪ ፈተናዎች ውስጥ የተካተቱት የሰዋስው ይዘት ጥያቄዎች አብዛኞቹ በተተኳሪ መርሀ ትምህርቶችና መማሪያ መጻሕፍት ውስጥ የተካተቱን ይዘቶች ሙሉ በሙሉ ባይሆንም አብዛኛውን የሰዋስው ይዘት እንዳካተቱ ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ በ2002 ዓ.ም. በተሰጠው ፈተና ውስጥ የምዕላድንና የቃልን አንድነት እና የስም መሙያን፣ በ2003 ዓ.ም. በተሰጠው ፈተና ውስጥ የአረፍተ ነገርን ስልት የሚወክል ጥያቄ እና በ2006 ዓ.ም. በተሰጠው ፈተና ውስጥ ደግሞ የስምና የግስ ገላጭን የሚወክሉ ጥያቄዎች በተተኳሪ መርሀ ትምህርቶችና መማሪያ መጻሕፍት ውስጥ ያልተካተቱ ይዘቶች በፈተናው ውስጥ ተካተው እንደሚገኙ ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ በፈተናዎቹ ውስጥ ተካተው የሚገኙት የሰዋስው ጥያቄዎች ይዘት በመርሀ ትምህርቶቹ እና በመማሪያ መጻሕፍቱ ውስጥ ከተሰጣቸው የትኩረት ደረጃ አኳያ ለየይዘቶቹ ተገቢ ውክልና እንዳልተሰጣቸው በሰነድ ፍተሻው ተረጋግጧል፡፡ ተተኳሪ ፈተናዎችም ከፈተና መርሆዎች አኳያ ሲፈተሹ ጠንካራ ጎናቸው የሚያመዝን ቢሆንም እንኳ ደካማ ጎንም ታይቶባቸዋል፡፡ በመጨረሻም በጥናቱ ተተኳሪ በሆኑ ፈተናዎች የሰዋስው ጥያቄዎች ይዘት ላይ የታዩት ደካማ ጎኖች ወደፊት በሚዘጋጁ ፈተናዎች ላይ እንዳይደገሙና ጥንቃቄ ለማድረግ ያመች ዘንድ አስተያየት ተሰንዝሯል፡፡amበሀገር አቀፍ ፈተናዎች ድርጅት ለአጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያከ2001 – 2006 ዓ.ም. በሀገር አቀፍ ፈተናዎች ድርጅት ለአጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ በተዘጋጁ የአማርኛ ቋንቋ ፈተናዎች ውስጥ የተካተቱ የሰዋስው ጥያቄዎች ይዘትና አቀራረብ ትንተናThesis