ዶ/ር ግርማ ገብሬልዩወርቅ እምሻው2023-12-152023-12-152022-07http://etd.aau.edu.et/handle/123456789/1051የዚህ ጥናታዊ ጽሁፍ ተቀዳሚ አላማ አማርኛ ቋንቋን በመማር ረገድ በወንድና ሴት ተማሪዎች መካከል ያለ ንጽጽር በጮሌ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዘጠነኛ ክፍል አማርኛ ቋንቋ ክሂል ችሎታ ምን እንደሚመስል መመርመር ነው።ይህም ማለት በወንድና ሴት የዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል በአማርኛ ቋንቋ ክሂል ችሎታ ተጨባጭ የሆነ ልዩነት መኖር አለመኖሩን መመርመርና ልዩነትም ካለ በሁለቱ ጾታዎች መካከል በምን ያህል ስፋት ይገኛል የሚለውን ለመለየት ነው። ይህ ጥናት በጾታዎቹ መካከል ያለውን አጠቃላይ የቋንቋ ክሂል ችሎታ ልዩነት ለመለካትየተጠቀመው የግንዛቤ መለያና የቃል ጽህፈት ሙከራዎችን ነው። ለጥናቱ በመረጃ ምንጭነት ያገለገሉት በጮሌ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚገኙ የዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች ናቸው። በ2015 ዓ.ም. በትምህርት ገበታ ላይ ከነበሩት አጠቃላይ የዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል 91 ወንድና 105 ሴት ተማሪዎች በተጠኚነት ተመርጠዋል።ለግንዛቤና ለቃል ጽህፈት ሙከራዎች ያገለግላሉ ተብለው የተመረጡት አራት ምንባቦች (ሁለት ለግንዛቤ መለያና ሁለት ለቃል ጽህፈት ሙከራ) በስራ ላይ ከመዋላቸው በፊት የጥናቱ ትኩረት ለሆኑት በዘጠነኛ ክፍል ደረጃ ለሚማሩ ተማሪዎች መመጠን አለመመጠናቸውን ለማረጋገጥ በተነባቢነት ቀመር (ፎግ ኢንዴክስ) መሰረት ተሰልተው የሚመጥኑ መሆናቸው ታውቋል። በዚህም መሰረት በወንድና ሴት የዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል በአጠቃላይ የቋንቋ ክሂል ችሎታ አንጻር ከግንዛቤ የሚገባ ልዩነት መኖር አለመኖሩን ለማረጋገጥ ተጠኚ ተማሪዎቹ በሁለቱ ሙከራዎች ያስመዘገቡት አማካይ ውጤትና ስታንዳርድ ዲቪዬሽን ከተተነተነ በኋላ የአጠቃላይ ውጤቱ በቲቴስት ቀመር መሰረት ተሰልቶ በግንዛቤ መለያና በቃል ጽህፈት የተመዘገበው ነጥብ በቅደም ተከተል 0.8509 እና 1.8505 ሲሆን ይህ ውጤት ደግሞ ልዩነት መኖሩን ለማረጋገጥ ከሚጠበቀው ዋጋ 1.9723 በታች ነው። በዚህም ማረጋገጥ የተቻለው በሴትና ወንድ ተማሪዎች መካከል በአማርኛ ቋንቋ አጠቃላይ ክሂል ችሎታ ከግንዛቤ የሚገባ ልዩነትአለመስተዋሉን ነው።amአማርኛ ቋንቋ ክሂል ችሎታአማርኛ ቋንቋን በመማር ረገድ በወንድና ሴት ተማሪዎች መካከል ያለ ንጽጽር በጮሌ ሁለተኛደረጃ ት/ቤት በ9ኛ ክፍል አማርኛ አፈፈት ተማሪዎች የቋንቋ ክሂል ችሎታ ላይ ያተኮረThesis