ካሳዬ, አለሙቀለሙ, አትክልት2021-05-042023-11-092021-05-042023-11-092001-06http://etd.aau.edu.et/handle/123456789/26303ይህ ጥናት በባህር ዳር ከተማ በአማራ ብሄራዊ ክልል ድምፅ በ“ሀሳብ ለሀሳብ” የመዝናኛ ራዲዮ ፕሮግራም ከጥቅምት 1/2001 እስከ የካቲት 20/2001 ዓ.ም የተላለፉትን የፍቅር ግጥሞች፣ ቀልዶች፣ የፍቅር አባባሎች፣ ደብዳቤዎችና ሙዚቃዎችን ይዘትና ጥልቃቸውን ለመተንተን ተሞክሯል:: የ“ሀሳብ ለሀሳብ” የመዝናኛ ፕሮግራም በአንድ መልኩ ስለወጣቶች በፍቅር ዙሪያ የሚወያዩበትና የሚዝናኑበት የፕሮግራም አይነት ነው:: ይህም አጥኚውን ያነሳሱት ነገሮች የሚከተሉት ናቸው፤ ወጣቶች በስልክና በደብዳቤ የሚሳተፉበት የፕሮግራም አይነት በመሆኑ ነው:: ስለሆነም አጥኚው ጥናቱን ከማጥናቱ በፊት በዚህ ፕሮግራም ተሳታፊ ስለነበር ሊያጠና ችሏል:: በመሆኑም በዚህ የመዝናኛ የራዲዮ ፕሮግራም የተላለፉትን በራዲዮ ጣቢያው ድምፅ ላይቫራሪ በመግባትና በማዳመጥ እንዲሁም ስለራዲዮ ፕሮግራም የሚያወሱትን መፅሀፍ በማንበብ ጥናቱ ውጤታማ ሆኖ እንዲጠና አጥኚውን ረድቶታል:: በመጨረሻም የራዲዮ አዘጋጆችን ቃለመጠይቅ በማድረግ በራዲዮ የድምፅ ላይቫራሪ በመግባት በማዳመጥና በመፃፍ 20 ያህሉን በፕሮግራሙ የተላለፉትን የፍቅር ግጥሞች፣ ሙዚቃዎች፣ የፍቅር አባባሎች፣ ደብዳቤዎችና ቀልዶችን በመሰብሰብ ከቅርፅና ይዘት አኳያ ሰፋ ያለ ማብራሪያ በመስጠት ለመተንተን ተሞክሯል::amበባህር ዳር ከተማ የአማራ ብሄራዊ ክልል ድምፅ መደበኛ ራዲዮበባህር ዳር ከተማ የአማራ ብሄራዊ ክልል ድምፅ መደበኛ ራዲዮ በሀሳብ ለሀሳብ የመዝናኛ ፕሮግራም አደረጃጀትና አቀራረብ በተመረጡ ናሙናዎች ምሳሌነትThesis