ፕሮፈፌሰር ጌታሁን አማረሞገስ አዲስ2024-11-072024-11-072016-12https://etd.aau.edu.et/handle/123456789/3565የዚህ ጥናት አሊማ በጉራጌ ዞን በእዣ ወረዲ በየዋኸንየ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለዘጠነኛ ክፍል ተዘጋጅተው የቀረቡ አማርኛ ቋንቋ የማጠቃለያ ፈተናዎችን የይዘት ተገቢነት መገምገም ነው፡፡ ጥናቱ አይነታዊ የአጠናን ዘዴን የተከተለ ሲሆን ገምጋሚ የምርምር ንድፍን መሰረት አድርጎ ተሰናድቷል፡፡ የንሞና አመራረጡ አመቺ ስልትን የተከተለ ነው፡፡በፈተና የሰነድ ፌተሻ የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያነት የተገኙትነን መረጃዎች መተንተን ተችሎል፡፡ ትንተናዎቹም በገለጻዊና በትረካዊ መልክ ቀርበዋል፡፡፡፡ የጥናቱ ግኝቶችም እንደሚያሳዩት የተዘጋጁት ምዘናዎች የተማሪዎችን የቋንቋ ችሎታ በሚገባ የማይመዝኑ፣የአደረጃጀት ችግር ያለባቸው፣አውዳዊ ያልሆኑ፣ መስፈርቶች ያልተዘጋጁላቸው፣ ከችሎታ መለኪያ ፈተና አዘገጃጀት መርሆዎች አንፃር ውስንነት ያለባቸው እንደሆኑ መረጃዎቹ አመሊክተዋል፡፡ ስለሆነም የሚዘጋጁት የቋንቋ ፈተናዎች ከመርሃ ትምህርቱና መማሪያ መፅሀፈ ጋር ያላቸው ትስስር የተሻለ ቢሆንም ሁለንም የቋንቋ ትምህርት ይዘቶች በትክክሌ አካቶ ከማቅረብ አንፃር፣ የተመረጡት የይዘቶች ተገቢነት፣ አደረጃጀት፣ ነጠላ ከመሆን፣ በአውድ ከመቅረብ፣ ከማሳሳት ሀይሌ፣ በጥያቄዎቹ ግንድ ላይ ከመቅረብ፣ ሁለን አካታች ከመሆን፣ ካልቸው የቁጥብነት ሁኔታ፣ ውስንነቶች እንዲለባቸው መደምደሚያ ላይ የተደረሰ ሲሆን የቀጣይ የመፌትሄ ሃሳቦችም ተቀምጠዋል፡፡amከ2013-2014ዓ.ም የአማርኛ ቋንቋ ማጠቃለያ ፈተናዎች የይዘት ተገቢነት ግምገማ በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ በየዋኸንየ አጠ/2ኛ/ደ/ እና መሰናዶ ትምህርት ቤት በዘጠነኛ ክፍል ተተኳሪነትThesis