AAU Institutional Repository

የትረካ ድምጽ እና አተኩሮ በተመረጡ የአማርኛ የወንጀል ክትትል ረጅም ልቦለዶች

Show simple item record

dc.contributor.advisor ፍቅሬ (ፒ.ኤች.ዲ), አየለ
dc.contributor.author ጌትነት, ዮሴፍ
dc.date.accessioned 2021-01-11T11:34:21Z
dc.date.available 2021-01-11T11:34:21Z
dc.date.issued 2012-04
dc.identifier.uri http://etd.aau.edu.et/handle/123456789/24604
dc.description.abstract ይህ ጥናት የትረካ ድምጽ እና አተኩሮ በተመረጡ የአማርኛ የወንጀል ክትትል ልቦለዶች በሚል ርእስ የተሰራ ነው፡፡የወንጀል ክትትል ልቦለድ ምስጢራዊ በሆኑ ከባድ የወንጀል ድርጊቶች ላይ በመመስረት ወንጀል ፈጻሚው ማን እንደሆነ፣ወንጀሉን ለምን፣የት፣መቼ እና እንዴት እንደፈጸመው በልዩ ልዩ የምርመራ ዘዴዎች፣በመርማሪው ችሎታ፣ክሂልና ጥበብ ወንጀለኛው የሚጋለጥበትንና ለፍርድ የሚቀርብበትን ሂደት የሚተርክ የሥነ ጽሑፍ አይነት ነው፡፡ የጥናቱ አቢይ ዓላማም ደራስያኑ የወንጀል ክትትል ታሪካቸውን ለአንባቢ ለማቅረብ ከመረጧቸው የትረካ ስልቶች ውስጥ የትረካ ድምጽ እና አተኩሮው እንዴት እንደቀረበና ለምን አገልግሎት እንደዋለ ይህም ለልቦለዶቹ ታሪክ ያበረከተው ኪናዊ ፋይዳ እና ያመጣው ድክመት ምን እንደሆነ መርምሮና ተንትኖ ማሳየት ነው፡፡ልቦለዶቹ የተመረጡት ከ1970ዎቹ እስከ 2004 ዓ.ም ድረስ ከታተሙ ረጅም የወንጀል ክትትል ልቦለዶች ውስጥ በዓላማ ተኮር የናሙና ዘዴ ከየአሰርቱ አንድ በመምረጥ ነው፡፡ልቦለዶቹም የይልማ ሀብተየስ አጋጣሚ (1979) የፈቃደ ዮሐንስ ሠንሠለት (1983)፣የገስጥ ተጫኔ የፍቅር ቃንዛ (1992) እና የጌቱ ሶሬሳ የአመጻ ብድራት(2004)ናቸው፡፡ ጥናቱ ይዞት የተነሳውን ዓላማ ለማሳካትና ጥያቄዎችንም ለመመለስ ከቀዳማይና ከካልአይ የጽሁፍ ምንጮች በተገኙ አይነታዊ መረጃዎች ላይ የጽሑፍ የትንተና ዘዴን (text analysis) ተጠቅሟል፡፡ከትንተናው እንደታየው የአጋጣሚ፣የሠንሠለትና የፍቅር ቃንዛ ትረካ የቀረበው በታሪኩ ድርጊት ውስጥ ምንም አይነት ተሳትፎ በሌላቸው ውጫዊና ድብቅ ተራኪዎች ሲሆን የአመጻ ብድራት ተራኪ ግን የታሪኩ አካልና የድርጊቱ ዋና ተሳታፊ በመሆኑ በገጸ ባህርይ አትኳሪው አማካኝነት የቀረበ ነው፡፡ልቦለዶቹ ውስጥ ጊዜ የሀላፊ፣የአሁን፣ግጥምጥሞሽና ስግሰጋ በተባሉ መንገዶች ተገልጿል፡፡ በሁሉም ልቦለዶች ውስጥ የወንጀል ክትትሉ የቀረበው በአሁን ጊዜ ሲሆን የገጸ ባህርያቱን ያለፈ ማንነትና መቼታቸውን ለማሳየት ደግሞ የሀላፊ ጊዜ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ተራኪዎቹ ግጥምጥሞሽንና ስግሰጋን የተጠቀሙት ለጭብጡ ማጠናከሪያ፣ለትልሙ ማደርጃ፣ለትዕይንት መፍጠሪያ፣ለምርመራ ቴክኒክ ፣ ለአንባቢ ተጨማሪገጠመኝ ለመስጠትና የንባብ ጉጉት መፍጠሪያ ብልሀት አድርገው ነው፡፡ የአጋጣሚ ፣ የሠንሠለትና የአመጻ ብድራት ተራኪዎች በእውቀትና በመረጃ ላይ ተንተርሰው ታሪካቸውን በማቅረባቸው የተአማኒነት ጥያቄ አልተነሳባቸውም፡፡የፍቅር ቃንዛ ልቦለድ ተራኪ የልቦለዱን ዘር ባህርይ ፣የአጻጻፍ ልማድና የአንባቢውን ባህል፣ወግ፣ልምድና እሴት ባለመጠበቁ ይህንንም ማፈንገጥ እንደ አንድ የትረካ ብልሃት ሊጠቀምበት ባለመፍቀዱ ተአማኒ ሊሆን አልቻለም፡፡ የልቦለዱ ትረካዎች ከጅምራቸው እስከ ፍጻሜያቸው የሀዘን ድባብ ያጠላባቸው ናቸው፡፡ ሀዘን፣ ልቦለዶቹ ውስጥ ብቻውን የመጣ ስሜት አይደለም፡፡ ጸጸትን፣ ንዴትን፣ ተስፋ መቁረጥን ፍርሀትን፣ቅናትን፣ቁጭትና ቂም በቀልን አስተሳስሮ የተከሰተ ነው፡፡የእነዚህ ጊዜያዊና ዘላቂ ስሜቶች አብሮነትና መተሳሰር ነው የንባብ ጉጉትን የፈጠረልን፡፡ ልቦለዶቹ ውስጥ ርዕዮተ ዓለም የተገለጸባቸው መልኮች መደብ፣ሥልጣን፣ጾታዊ አድልኦ፣ጋብቻ፣ ሀይማኖት እና እሴት ናቸው፡፡ en_US
dc.language.iso am en_US
dc.publisher አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ en_US
dc.subject የአማርኛ የወንጀል ክትትል ረጅም ልቦለዶች en_US
dc.title የትረካ ድምጽ እና አተኩሮ በተመረጡ የአማርኛ የወንጀል ክትትል ረጅም ልቦለዶች en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record

Search AAU-ETD


Browse

My Account